የ2019 የአፍሪካ ዋንጫ በረመዳን ፆም ምክንያት ለአንድ ሳምንት ተራዝሟል፡፡
የ2019 የአፍሪካ ዋንጫ በረመዳን ፆም ምክንያት ለአንድ ሳምንት ተራዝሟል፡፡
የቶታል ካፍ 2019 የአፍሪካ ዋንጫ ዋና ባለቤት ካፍ እንዳስታወቀው፤ በረመዳን ፆም ምክንያት ለሙስሊም እግር ኳስ ተጫዋቾች ዕረፍት ለመስጠት ሲባል ውድድሩን ቀደም ሲል ሊያከናውንበት ከነበረው ሰኔ 15 ወደ ሰኔ 21/2019 መግፋቱን ይፋ አድርጓል፡፡
ውድድሩ ከሰኔ 15 እስከ ሀምሌ 13 ይካሄዳል ተብሎ ቀን የተቆረጠለት ቢሆንም፤ ለአንድ ሳምንት ያህል ተገፍቶ ከሰኔ 21 እስከ ሀምሌ 19/2019 እንደሚከናወን የቀድሞው የግብፅ ብሄራዊ ቡድን ተጫዋች እና የውድድሩ ዳይሬክተር መሀመድ ፋድል አስታውቋል፡፡
ፋድል ውድድሩ የሚጀምርበት ቀን በአንድ ሳምንት እንዲራዘም የሆነው ከሞሮኮ፣ ቱኒዚያ፣ እና አልጄሪያ በመጣ ጥያቄ መሆኑን እና ተጫዋቾቻቸው ከረመዳን መጠናቀቅ በኋላ ዕረፍት እንዲያገኙ በሚል መሆኑን ተናግሯል፡፡
የአፍካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) የውድድሩ የዕጣ ድልድል ሚያዚያ 12/2019 ይፋ እንደሚሆንም አያይዞ ይፋ አድርጓል፡፡
የረመዳን ፆም የእስልምና ዕምነት ተከታዮች ከፅሀይ መውጫ እስከ ፅሀይ መግቢያ ሰዓት ድረስ ምግብና ውሃ ከመውሰድ ታቅበው ፈጣሪያቸውን የሚያመሰግኑበት ወቅት ሲሆን ከግንቦት ወር መጀመሪያ እስከ ሰኔ ወር መጀመሪያ ድረስ የሚዘልቅ ተናፋቂ ሀይማኖታዊ ትልቅ ክንውን ነው፡፡
የዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ለመጀመሪያ ጊዜ ከጥር ወደ ሰኔ የተሸጋገረ ሲሆን የተሳታፊ ሀገራትን ቁጥርም ከ16 ወደ 24 ከፍ እንዲል ተደርጓል፡፡
ካሜሮን ልታስተናግድ የነበረውን ውድድር ካፍ የውድድረድ ዝግጅትሽ አመርቂ አይደለም በማለት የአዘጋጅነቱን ፍቃድ ከምዕራብ አፍሪካዊቷ ነጥቆ ለሰሜን አፍሪካዊቷ ሀገር ግብፅ አሳልፎ የሰጠ መሆኑ ይታወቃል፡፡
BBC