loading
የ81 የፖለቲካ ድርጅት አመራሮች ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር ተወያዩ

አርትስ 18/03/2011

ውይይቱም ቀጣዪን ምርጫ ነጻና ፍትሃዊ ለማድረግሊወሰዱ ስለሚገባቸው የሪፎርም ስራዎችላይ ያተኮረ ነበር፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩም  ከተፎካካሪ ፓርቲዎቹ ጋር በነበራቸዉ  ዉይይት መንግስትም ተፎካካሪ ፓርቲዎቸም ለምርጫዉ ነጻና ዲሞክራሲያዊነት  የጋራ ኃላፊነታቸዉን ሊወጡ ይገባል ብለዋል፡፡

ጠ/ሚኒስትሩ ለተፎካካሪ ፓርቲዎቹ የምንሰራው ስራ አገራችንን የማያፈርስ መሆን አለበት ብለዋል፡፡ በተጨማሪም የተፎካካሪ ፓርቲዎች ልዩነት ከህዝብና ከአገር በታች በመሆኑ በመወያየት የጋራ ሀሳብ መያዝ ይቻላል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ በሃሳብ መሰባሰብን አፅንኦት በሰጡበት ውይይት ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎቹም ከፓርቲዎች ቁጥር፣ የህገመንግስት ማሻሻያ ሃሳብ ፣ከመጪው ምርጫ በፊት የህግ የበላይነትን ማረጋገጥን በተመለከተ ጥያቄና አስተያየት ሰጥተዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *