loading
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አመራሮች የምርጫ ቦርድን የምርጫ ዝግጅት ጎበኙ::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2013 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አመራሮች የምርጫ ቦርድን የምርጫ ዝግጅት ጎበኙ::የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎና የምክር ቤት አመራሮች የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ ቅድመ ዝግጅትን እየጎበኙ ነው።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛው አገር አቀፍ ምርጫ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የመከላከያ መንገዶችን በመተግበር እንዲካሄድ ከጤና ሚኒስቴር የቀረበለትን ምክረ ሃሳብ በተጨባጭ በማጤን መወሰኑ ይታወሳል።በዚህም ምክር ቤቱ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ተገቢውን የመከላከያ እርምጃዎች እየወሰደ በ2013 ዓ.ም ስድስተኛውን አገራዊ ምርጫ ለማካሄድ ስራውን እንዲጀምር ወስኖ ነበር።

በውሳኔው መሰረት እየተከናወኑ ያሉ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን የህዘብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤው አቶ ታገሰ ጫፎና አመራሮች ዛሬ በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቅጠር ግቢ ተገኝተው እየጎበኙ ነው።በእዚህም አጠቃላይ የቁሳቁስ ዝግጅቶችን ተመልክተዋል።ከእዚህ በፊት የነበረውን የድምጽ መስጫ ኮሮጆን ጨምሮ ለ6ኛው አገር አቀፍ ምርጫ የተዘጋጁ ሌሎች ዘመናዊ ቁሶችን በማነጻጸር እየጎበኙ ነው።ከጉብኙቱ በኋላም አፈ ጉባኤው አቶ ታገሰ ጫፎና የምክር ቤቱ አመራሮች ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሥራ ኃላፊዎች ግብረ መልስ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *