loading
የህዳሴ ግድቡ ሁሉም ሥራዎች በተያዘላቸው ዕቅድ መሰረት እየተከናወኑ መሆናቸው ተገለፀ::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ7፣ 2012 የህዳሴ ግድቡ ሁሉም ሥራዎች በተያዘላቸው ዕቅድ መሰረት እየተከናወኑ መሆናቸው ተገለፀ:: የግድቡ አጠቃላይ የሲቪል ሥራ አፈጻጸም 88 ነጥብ 5 በመቶ፤ የግንባታ ፕሮጀክቱ ደግሞ 75 በመቶ መድረሱን የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጅነር ክፍሌ ሆሮ ገልጸዋል። ኢንጅነር ክፍሌ እንደገለጹት ከመጀመሪያው ዙር የግድቡ ውሃ ሙሌት በኋላም የግንባታ ሥራዎች በተያዘላቸው ዕቅድ መሰረት እየተከናወኑ ነው።

ግድቡ ውሃ መያዝ መጀመሩም ከዚህ ቀደም ሲሠሩ የነበሩ ሥራዎችን አፈጻጸም ከፍ እንዲል ማስቻሉን ጠቅሰዋል። በዚህም የዋናው ግድብ ሥራ፣ የኮርቻ ግድብ፣ የጎርፍ ማስተንፈሻና የኃይል ማመንጫ ሥራዎችን የሚያጠቃልለው የግድቡ የሲቪል ሥራ 88 ነጥብ 5 በመቶ፤ የኤሌክትሮ መካኒካል ሥራዎች ወደ 46
በመቶ፣ የብረታ ብረት ሥራው ደግሞ ወደ 33 በመቶ ከፍ ማለቱን ነው የገለጹት። አጠቃላይ የግድብ ግንባታ ፕሮጀክቱም ወደ 75 በመቶ ከፍ ማለቱን ነው ዋና ሥራ አስኪያጁ የተናገሩት። ሁለት ተርባይኖችን በመጠቀም በቀጣዩ ዓመት ኃይል ለማመንጨት የግድቡ ቀኝና ግራ የብረታ ብረት ሥራዎችና የጀኔሬተር ተከላ መከናወኑንም ኢንጅነር ክፍሌ ለኢትጵያ ፕሬስ ድርጅት ተናግረዋል። ኢዜአ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *