loading
የህዳሴው ግድብ የሰላም ፕሮጀክት ነው” ደቡብ-ሱዳን

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 14፣ 2013  ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ለሶስትዮሽ ድርድሩ ህብረቱ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ተስፋ አለን አሉ፡፡

አቶ ደመቀ “ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔ” መርህ መሰረት የሶስትዮሽ ድርድሩ ውጤታማ እንዲሆን የአፍሪካ ህብረት ሚናው አጠናክሮ እደሚቀጥል ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።አቶ ደመቀ የግድቡ ሁለተኛ ዙር የውኃ ሙሊት በተያዘለት ጊዜ እንደኪካሄድም አብራርተዋል፡፡

አቶ ደመቀ ይህን ያሉት “የናይል ፍትሐዊ አጠቃቀም፣ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ለክልላዊ ትብብር ያለው ሚና” በሚል ርእሰ ጉዳይ በተዘጋጀው የበይነ መረብ ውይይት ላይ ነው፡፡

በውይይቱ በጎረቤት ሀገራትና ታላላቅ ሐይቆች ክልል የሚገኙ የኢፌዲሪ ሚሲዮኖች ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዋና መስሪያ ቤት ጋር በመተባበር ነው የተዘጋጀው፡፡

የደቡብ ሱዳን ምክትል የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ጉዳዮች ሚኒስትር ደንግ ዳው ደንግ ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግ የሰላም ፕሮጀክት መሆኑን ገልጸዋል።  የሀገራቸው ፓርላማ በቅርቡ የናይል ስምምነት ማዕቀፍን እንደሚያጸድቅም አስታውቀዋል።

በተካሄደው የበይነ መረብ ውይይትም የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር የቴክኒክ ኮሚቴ ሰብሳቢ ኢንጂነር ጌዲዮን አስፋውና ሌሌች የዘርፉ ባለሙያዎች የውይይት መነሻ ጽሑፍ አቅርበዋል። መረጃው የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ነው

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *