loading
የመስቀል አደባባይና የባህረ ጥምቀት ቦታዎች ጥበቃ እንዲደረግላቸዉ ሲኖዶሱ አሳሰበ::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 23፣ 2013 የመስቀል አደባባይና የባህረ ጥምቀት ቦታዎች ጥበቃ እንዲደረግላቸዉ ሲኖዶሱ አሳሰበ:: ከሰኔ 14 ጀምሮ እስከ ሐምሌ 4 ቀን የሚቆይ የምህላ ፀሎት እንዲደረግ ቅዱስ ሲኖዶስ አወጀ፡፡ መጪው ሀገራዊ ምርጫ በኢትዮጵያዊ ጨዋነት በአንድነትና በሰላም እንዲጠናቀቅ በመላ
ኢትዮጵያ ፀሎተ ምህላ እንዲደረግ ቅዱስ ሲኖዶስ ባሳለፈው ወሳኔ አስታውቋል ገዢው ፓርቲም ሆነ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለህዝቡ የሚጠቅመውን ሰላማዊ መንገድ እንዲከተሉ ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪ አቅርቧል፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ከግንቦት 17 ቀን 2013 ጀምሮ ለስድስት ቀናት ሲያካሄድ የነበረውን አመታዊ ስብሰባ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ አጠናቋል ፡፡ ሲኖዶሱ ሀገራችን ኢትዮጵያ በሽግግር ላይ የምትገኝ ቀጣይ ሀገራዊ ምርጫ ለማካሄድ በከፍተኛ ዝግጅት ላይ በመሆኗ ገዢው ፓርቲም ሆነ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለሀገር እና ለህዝብ የሚጠቅመውን ሰላማዊ መንገድ እንዲከተሉ ህዝቡም ውጤቱን በፀጋ እንዲቀበል የሰላም ጥሪ
አቅርቧል፡፡

በተለይም በአለም አቀፍ ደረጃ በዩኔስኮ ተመዝግቦ የሚገኘውን የመስቀል አደባባይና የባህረ ጥምቀት ቦታዎች ልዩ እንክብካቤና ጥበቃ ሊደረግለት ስለሚገበ አሁንም መንግስት ለጉዳዩ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ሲኖዶስ በአጽንኦት አሳስቧል፡፡ በሌላ በኩል በተለያዩ አካባቢዎች በተፈጠሩ ግጭቶች ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉትን በመርዳት እስካሁን የጠፋውን የሰው ህይወት በቁጥርና በአይነት ተለይቶ ለቅዱስ ሲኖዶሱ እንዲቀርብ ነው ጉባኤው ያሳሰበው ፡፡

ሲኖዶሱ ከህዳሴው ግድብ ጋር በተያያዘ ሀገራችን ሌሎች ሀገራት የደረሱበት እንድትደርስ ብሎም ዜጎች ከጨለማ ወደ ብርሃን እንዲወጡ ግድቡ የመጨረሻው ምዕራፍ እንዲደርስ መላው ህዝብ ርብርብ እንዲያደርግ ነው ጥሪ የቀረበው ፡፡ መላው ህዝብም ከምንግዜውም በላይ አንድነቱን በማጠናከረ አንዳንድ ሀገራት በሀገራችን እያደረጉ ያለውን ጣልቃ ገብነት በመቃወም የበኩሉን አንዲወጣ ጉባኤው ጥሪ አቅርቧል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *