የመቐለ ከተማ መጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን የማስፋፊያ ፕሮጀክት ተመረቀ
የመቐለ ከተማ መጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን የማስፋፊያ ፕሮጀክት ተመረቀ
አርትስ 26/02/2011
ፕሮጀክቱን የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር ደብረ ጽዮን ገ/ሚካኤልና የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጅር ስለሺ በቀለ እንዲሁም ሌሎች የፌደራልና የክልል መንግሥታትየሥራ ኃላፊዎችና የአካባቢው ነዋሪዎች በተገኙበት ተመርቋል።
የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክቱ ሁለት ክፍሎች ያሉት ሲሆን፥ የመጀመሪያው ክፍል በድምሩ 156 ሊትር በሰከንድ ወይም 12 ሺህ 355 ሜትር ኩዩብ በቀን የማምረት አቅም ያለው ሲሆን፥ 6 የውሃጉድጓዶችና የ33 ነጥብ 9 ኪሎ ሜትር መስመር ዝርጋታ እንደተከናወነ የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር አስውቋል።
የሚኒስቴሩ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ብዙነህ ቶልቻ ለፋና እንደገለፁት፥ የሁለተኛው ክፍል በድምሩ 121 ሊትር በሰከንድ ወይም 9 ሺህ 583 ሜትር ኪዩብ በቀን የማምረት አቅም ያላቸው 4 የውሃጉድጓዶችና 21 ነጥብ 45 ኪሎ ሜትር መሥመር ዝርጋታ ይይዛል ተብሏል።
በዚህ ፕሮጀክት እያንዳንዳቸው 50 ሊትር በሰከንድ የመግፋት አቅም ያላቸው የ10 ውሃ ፓምፖች ተካላ የተካሄደ ሲሆን፥ በድምሩ 7 ሺህ 500 ሜትር ኪዩብ የመያዝ አቅም ያላቸው አምስት የተለያዩ ጋኖችግንባታ ተከናውኗል፡፡
ይህ ፕሮጀክት ከጉድጓድ የሚመነጨውን የውሃ መጠን ፣ በየመግፊያ ጣቢያዎቹና ማጠራቀሚያ ጋኖች የሚደርሰውን የውሃ መጠን፣በውሃ ውስጥ ያለውን የክሎሪን መጠን ማወቅ የሚያስችል የስካዳ ሲስተምተዘርግቶለታል፡፡
ፕሮጀክቱ የከተማውን የውሃ ሽፋን 68 ነጥብ 4 በመቶ እንደሚያደርሰው የከተማው ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ኃላፊ አቶ ጊዳና አበበ ተናግረዋል፡፡
የከተማዋን የውሃ አቅርቦት ለማሻሻል ለፕሮጀክቱ የዓለም ባንክ፣ የከተማው አስተዳደር፣ የውሃ ሀብት ቢሮ እና የመቐለ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድጋፍ ማድረፋቸው ተጠቁሟል።