የመንገድ ፈንድን ኤጀንሲ ደረሰኝ በማስመሰል ሀሰተኛ ሰነዶችን በማዘጋጀት መንግስት ማግኘት የሚገባውን ገቢ እያጣ እንደሆነ ገለፀ፡፡
አዲስ አበባ፣ነሐሴ 20፣ 2012 የመንገድ ፈንድን ኤጀንሲ ደረሰኝ በማስመሰል ሀሰተኛ ሰነዶችን በማዘጋጀት መንግስት ማግኘት የሚገባውን ገቢ እያጣ እንደሆነ ገለፀ፡፡ ኤጀንሲዉ ለአርትስ በላከዉ መግለጫ እንዳስታወቀዉ ፤ለመንገድ ፈንድ በአዋጅ ከተለዩ የገቢ ምንጮች አንዱ ክብደትን መሰረት ካደረገ አመታዊ የተሽከርካሪዎች ፈቃድ ማደሻ ክፊያ የሚገኝ ገቢ ነው እሱም እየተጭበረበረ ነዉ ብሏል፡፡
ይሄንን ገቢ ከኢትዮጵያ ፖስታ ቤት ጋር የመንግድ ፈነደ ጽ/ቤት ባደረገው ስምምነት መሰረት በፖስታ ቤት ቅርንጫፎች በኩል ተሰብስቦ በፓስታ ቤቱ ዋናው መስሪያ ቤት በኩል ከተጠቃለለ በኋላ ወደ መንገድ ፈንድ ገቢ ይደረጋል፡፡ ሆኖም አንዳንድ ኃላፊነት የጎደላቸው አካላት የመንገድ ፈንድን ደረሰኝ በማስመሰል ሀሰተኛ ሰነዶችን በማዘጋጀት መንግስት ማግኘት የሚገባውን ገቢ በአግባቡ እንዳይገባ በማድረግ ወንጀል እየፈጸሙ ስለመሆኑ ለመንገድ ፈንድ ጽ/ቤት ጥቆማ እንደደረሰዉ ገልጿል፡፡
ይሄንኑ ለማስቀረት እንዲቻል ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የእርምት እርምጃዎችን የመውሰድና ክብደትን መሰረት ያደረገ አመታዊ የተሽከርካሪዎች ፈቃድ ማደሻ ክፊያ አሰራርን የማዘመን ስራዎች በመሰራት ላይ ይገኛሉ ብለዋል ኤጀንሲዉ፡፡
በመሆኑም ሀሰተኛ ደረሰኝ በማዘጋጀትም ሆነ እነዚያን ደረሰኞች ጥቅም ላይ በማዋል ወንጀል በምፈጽም ባለተሽከርካሪ ላይ ሕጋዊ እርምጃዎች መውሰድ የተጀመረ መሆኑንና እድሳት ከተደረገም በኋላ ኦዲት የማድረግ ሥራ የሚሰራ መሆኑን አውቆ ማንኛው ባለተሽከርካሪ ትክክለኛውን ደረሰኝ ከፖስታ ቤት ብቻ በመውሰድ ክፊያውን እንዲፈጽም ኤጀንሲዉ አሳስቧል፡፡