loading
የማይናማር የጦር ጀኔራሎች በዘር ማጥፋት ወንጀል ሊጠየቁ ነው፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባደረኩት ምርመራ በማይናማር የሮሂንጊየያ ሙስሊሞች ላይ የተፈጸመው የጅምላ ጭፍጨፋ ዘር ማጥፋትን ያለመ እንደሆነ ደርሸበታለሁ ብሏል፡፡
ዘ ኢንዲፔንደንት እንደዘገበው ለተፈጸመው ወንጀል ቀጥተኛ ትእዛዝ በመስጠት እጃቸው አለበት የተባሉት የሀገሪቱ የመከላከያ አዛዥና አምስት ሹሞቻቸው በህግ ፊት ቀርበው መጠየቅ አለባቸው ብሏል ድርጅቱ ፡፡
ድጅቱ በሪፖርቱ እንዳስታወቀው የማይናማር ወታደሮች በንጹሀን ዜጎች ላይ የፈጸሙት የግድያና በርካታ መንደሮችን በጅምላ የማቃጠል ተግባር ከተለመደው የደህንነት ስጋት ያለፈ አንድን ዘር ሆን ብሎ የማጥፋት ዓላማ ያለው ነው፡፡
ለዚህ ደግሞ የአውንግ ሳን ሱኪ አስተዳደር ማድረግ የሚገባውን ንጹሀን ዜጎችን ከአደጋ የመከላከል ሀላፊነት በአግባቡ አልተወጣም፡፡ ይባስ ብሎም ይህን ጥፋት የሚያባብሱ የጥላቻ ንግግሮችና ቅስቀሳዎችን በመፍቀድ የውጤቱ ተባባሪ ሆኗል ሲል በሪፖርቱ ገልጿል፡፡
በማይናማር ይኖሩ የነበሩ ከ700 ሽህ በላይ የሮሂንጊያ ሙስሊሞች ከሀገሪቱ የጸጥታ ሀይሎች የሚደርድባቸውን ጥቃት ለመሸሽ በጎረቤት ባንግላዲሽ በጥገኝነት ኑሯቸውን እየገፉ ይገኛሉ፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *