loading
የምርጫ ቦርድ የምርጫ ኮሚሽን መደረግ አለበት ተባለ

አርትስ 13/03/2011

ይህ የተባለው የምርጫ ቦርድ አወቃቀር እና ምርጫ አስፈፃሚ አካላት ማሻሻያ ሃሳቦች ላይ ውይይት በተደረገበት ወቅት ነው፡፡

በውይይቱ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ፣የማሻሻያ ጥናቱን ያቀረቡት አካላት እና ከሌሎች ማህበራት እና ድርጅቶች የተወጣጡ  ተሳታፊዎች ተገኝተዋል ፡፡

ተሳታፊ ፓርቲዎች እንደገለፁት የምርጫ አስተዳደር ተቋሙ  አወቃቀር ተዘርግቶለት እስከታች እንዲሰራ የምርጫ ኮሚሽን መደረግ አለበት ብለዋል፡፡

ጥናቱን ካቀረቡት  ውስጥ ዶክተር ሲሳይ አለማየሁ  በምርጫ አስፈፃሚው አካል ወይም በምርጫ ቦርዱ አወቃቀር ፣የአመዘጋገብ ሂደት ፣የምርጫ ቦርዱ አሁን ያለው አቅም እና የኮሚቴዎች አወቃቀር እና ከምርጫ አስፈፃሚዎች እና ታዛቢዎች ጋር የተያያዘ ጥናት መደረጉን ተናግረዋል፡፡

በቦርዱ ክፍተቶች እና የአፈፃፀም ሂደቶች ዙሪያ ጥናቶች ቀርበው ከተሳታፊዎች ጋር ውይይት የተደረገ ሲሆን በውይይቱም ቦርዱ ቋሚ ኮሚቴ እንደሌለው እና ከ ሶስት መቶ ሺ የሚበልጡ የምርጫ አስፈፃሚዎች እና ታዛቢዎች  ምልመላ የሚደረገው ምርጫው ሲቃረብ መሆኑ የምርጫውን ግልፅነት እና ተጠያቂነት ጥያቄ ውስጥ የሚከሰት ነው ተብሏል፡፡

በውይይቱ የተገኙት ፓርቲዎች  በበኩላቸው የቦርዱ የአደረጃጀት እና የአስፈፃሚ አካል አወቃቀር ምርጫው ፍትሃዊ እና ግልፅ እንዳይሆን አድርጎታል ብለዋል

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *