loading
የምዕራብ አፍሪካ ኢኮኖሚ ማህበረሰብ ኢኮዋስ በማሊ የአንድነት መንግስት እንዲመሰረት ጥሪ አቀረበ::

አዲስ አበባ፣ሐምሌ21፣ 2012 የምዕራብ አፍሪካ ኢኮኖሚ ማህበረሰብ ኢኮዋስ በማሊ የአንድነት መንግስት እንዲመሰረት ጥሪ አቀረበ:: የቀጠናው ሀገራት መሪዎች በማሊ እየተባባሰ ለመጣው የአለመረጋጋት ችግር መፍትሄ ለማፈላለግ የሚያደርጉት ጥረት እስካሁን ይህ ነው የሚባል ውጤት እንዳላስመዘገበ ይነገራል፡፡ሰሞኑን ያደረጉት ስብሰባም በሀገሪቱ ጎራ ለይተው ግጭት ውስጥ የገቡትን ወገኖች ማስማማት አቅቷቸው ውይይታቸው ያለውጤት ነበር የተበተነው፡፡ አልጀዚራ እደዘገበው ኢኮዋስ በተቃራኒ ጎራ የቆሙት ወገኖች መስማማት የማይችሉ ከሆነ ማዕቀብ ሊጥል እንደሚችል አስጠንቅቋል፡፡
አስራ አምስት የምእራብ አፍሪካ ሀገራ መሪዎች በቪዲዮ ኮንፈረንስ ባደረጉት ምክክር ከፕሬዚዳንት ኢብራሂም ቡበከር ኬታ ጎን መሆናቸውን የገለፁ ቢሆንም ሰላምን ለማምጣት ሲባል ባአስቸኳይ የአንድነት መንግስት መመስረት አለበት ብለዋል፡፡ ተቃዋሚዎቹ በበኩላቸው ፕዚዳንቱ ህገ መንግስቱን በጣሰ መልኩ በስልጣን ላይ በመቆየታቸው እርምጃ ሊወሰድባቸው ይገባል የሚል ክስ አቅርበዋል፡፡ ከ15 ቀናት በፊት በማሊ ፕሬዚናንት ኬታን በመቃወም ጎዳና ላይ በወጡ ሰዎችና በፖሊስ መካከል በተፈጠረ ግጭት 11 ሰዎች መሞታቸው ይታወሳል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *