loading
የምዕራብ ኢትዮጵያ ኮማንድ ፖስት የአካባቢውን ሰላም ሲያውኩ የነበሩ 835 የኦነግ አባላትን በቁጥጥር ስር አውያለሁ አለ

የምዕራብ ኢትዮጵያ ኮማንድ ፖስት የአካባቢውን ሰላም ሲያውኩ የነበሩ 835 የኦነግ አባላትን በቁጥጥር ስር አውያለሁ አለ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልልና በምዕራብ ኦሮሚያ አካባቢዎች የተከሰተውን ግጭት ለመከላከል የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት ባወጣው መግለጫ ተስተጓጉለው የነበሩ የመንግስትና የግል ተቋማት፣ ማህበራዊና የንግድ እንቅስቃሴዎች ወደ መደበኛ ተግባራቸው መግባታቸውን አስታውቋል።

በህዝቡ ተሳትፎ ፀረ-ሠላም ኃይሎችን በማጋለጥ ለመንግስት አካላትና ለኮማንድ ፖስቱ ተጠቁመው የተዘረፉ ንብረቶች እንዲመለሱ እገዛ እየተደረገ ይገኛል ብሏል።

ኮማንድ ፖስቱ  ከአካባቢው ፖሊስ፣ ከሚሊሻና ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመሆን ከመጋዘን እና ከመንግስት ቢሮዎችና ግለሰቦች ዘርፎ ሲገለገልባቸው የነበሩ ቁሳቁሶችና የጦር መሳሪያዎችን መማረኩን ይፋ አድርጓል።

በተጨማሪም ኮማንድ ፖስቱ ለጠላት አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩ ተሽከርካሪዎች፣ የተለያዩ  ቁሳቁሶች፤  እንዲሁም ገንዘብ ማስመለሱን ተናግሯል፡፡

በአጠቃላይ 835 ታጥቀው የአካባቢውን ሰላም ሲያውኩ የነበሩ የኦነግ አባላትን በወሰደው እርምጃ በቁጥጥር ስር ማዋሉንም አስታውቋል።

ኮማንድ ፖስቱ በተለያዩ በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚለቀቁ የተዛቡና የተጋነኑ መረጃዎች ሚዛናቸውን እንዲጠብቁ አሳስቧል።

የመከላከያና የፀጥታ ኃይሉ ባልደረሰባቸው አካባቢዎች አልፎ አልፎ የሚከሰቱ የባንክም ሆነ ሌሎች የመንግስትና የግል ተቋማት ዝርፊያና የማቃጠል ሙከራዎች ቢኖሩም፥ ቁጥሩ የተጋነነ ነው ብሏል፡፡

ኮማንድ ፖስቱ ህይወት ለማትረፍ ስራ ቅድሚያ ሰጥቶ ከህዝቡ ጋር ጠንክሮ በመስራቱ በግልፅ የሚታይ ውጤት እንደተመዘገበ አስታውቋል።

ተዘረፉ ስለተባሉ ባንኮች  ወደፊት ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ተሳትፈውበት እና  ተጣርቶ ይፋ እንደሚሆንም አመልክቷል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *