የሞያሌ አዋሳኝ ድንበር ክልላዊ ጉባኤ እየተካሄደ ነው።
የሞያሌ አዋሳኝ ድንበር ክልላዊ ጉባኤ እየተካሄደ ነው።
ከኢትዮጵያና ኬንያ እና ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የተወከሉ ከፍተኛ ባለሥልጣናት በዘላቂ ሰላም ላይ የሚያተኩረው ጉባኤ ላይ ተሳታፊዎች ናቸው፡፡
ጉበኤው ለሁለት ቀናት የሚቆይ ሲሆን በአካባቢው በጉርብትና የሚኖሩ ማህበረሰቦች በመካከላቸው ያለውን ግጭትን አስወግደው በሰላም እና በመተሳሰብ እንዲኖሩ የማድረግ ዓላማ ያለው ነው፡፡
ባህላዊ የግጭት አፈታት ዘዴዎችን በመጠቀም እንዴት ሰላምን ማስፈን እንደሚቻልም ጉባኤተኞቹ በስፋት የሚመክሩበት አጀንዳ መሆኑን የሰላም ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡