loading
የሱዳን አመፅ ከአረብ አብዮት የተቀዳ ስለመሆኑ አልበሽር ፍንጭ ሰጡ፡፡

የሱዳን አመፅ ከአረብ አብዮት የተቀዳ ስለመሆኑ አልበሽር ፍንጭ ሰጡ፡፡

አልበሽር ይህን ያሉት በሀገራቸው አመፁ ከተቀሰቀሰ ወዲህ ሁለተኛ የውጭ ሀገር ጉብኝታቸውን በጎረቤት ግብፅ ባደረጉበት ወቅት ነው፡፡

ፕሬዝዳንቱ ነገሩን ከረአብ አብዮት ጋር ያገናኙት የዳቦ ዋጋ ጨመረብን ብለው ለተቃውሞ አደባባይ የወጡት ሰልፈኞች አጀንዳቸውን ቀይረው አልበሽር ከሰልጣን ይውረዱ ይህ ካልሆነ ግን  ወደ ቤት በማለታቸው ነው፡፡

የሱዳኑ ፕሬዝዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር 30 ዓመት በሚጠጋው የአስተዳደር ዘመናቸው እንዲህ ዓይነት ጠንካራ ተቃውሞ ደርሶባቸው አያውቅም ተብሏል፡፡

አልበሽር ተቃውሞው በተበባሰበት ሰሞን የኢኮኖሚ መሻሻያዎችን ለማድረግ ቃል ገብተው ነበር፡፡ ግን ደግመሞ  በሀገሪቱ የተከሰተው የውጭ ምንዛሬ እጥረት አላለውስ ቢላቸው ወደ ኳታር ተጉዘው የኳታሩን አሚር እርዳታ ጠይቀዋል፡፡

ይሁን እንጂ አሁን በሱዳን እየተነሳ  ያለው ጥያቄ የዳቦ ዋጋ ይቀንስ ሳይሆን አልበሽር ይውዱ የሚል ስለሆነ ኳታር እጇን ብትዘረጋ እና የተባለው ማሻሻያ ተግባራዊ ቢሆ እንኳ እርምጃውን የዘገየ ነዉ  ይላሉ ይላሉ የፖለቲካ አዋቂዎች፡፡

አልጀዚራ እንደዘገበው የግብፁ ፕሬዝዳንት አብደልታህ አልሲሲ ሱዳን ወደተረጋጋ ህይዎት እንድትመለስ አልበሽርን ለማገዝ ዝግጁነታቸውን ነግረዋቸዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *