የሱዳን የተቃውሞ ሰልፈኞች አልበሽር ከስልጣን ሳይወርዱ ወደ ቤት አንገባም ብለዋል
የሱዳን የተቃውሞ ሰልፈኞች አልበሽር ከስልጣን ሳይወርዱ ወደ ቤት አንገባም ብለዋል
የሱዳን የሞያ ማህበራት እና ሶስት የተቃዋሚ ፓርቲ ጥምረቶች በጋራ ባወጡት መገለጫ መላ ሀገሪቱን ያነቃነቀው ተቃውመው ፕሬዝዳንት ኦማር አልበሽር ስልጣናቸውን እስኪያስረክቡ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡
በአልበሽር ላይ ቁጣቸው የበረታው እነዚህ ሰልፈኞች ተቃውሟችን እውነተኛ እና ምክንያታዊ በመሆኑ ፕሬዝዳንቱ ይህን አውቀው ስልጣናቸውን ካላስረከቡ እኛ ለዓመታት ሰብንሰለፍ አይሰለቸንም ብለዋል፡፡
ሚድል ኢስት ሞኒተር እንደዘገበው በካርቱም እና በኡምዱርማን ከተሞች ለተቃውሞ የወጡ ሰዎች ከፖሊስ ጋር ግጭት ውስጥ ገብተው ነበር፡፡
መንግስት እኛን ለማስፈራራት የሚያደርገውን ጥረት ሁሉ እናውቃለን ግን ጥያቄያችን መልስ እስካላገኘ ድረስ አንበገርም ነው ያሉት፡፡
ከአንድ ወር በላይ የዘለቀው የሱዳን ተቃውሞ መነሻው የዳቦ ዋጋ በሶስት እጥፍ መጨመሩ ይሁን እንጂ የኋላኋላ ግን ፕሬዝዳንት አልበሽርን ከስልጣን ወደ ማውረድ አጀንዳነት ተቀይሯል፡፡
በሀገር ቤት የተነሳው ቀውስ ሳይበርድ ፕሬዝዳንት አልበሽር ወደ ኳታር አቅንተዋል፡፡ የጉዟቸው ዓላማም በሀገሪቱ የተከሰተውን የዋጋ ንረት ለማብረድ የሚያስችል እርዳታ ለመጠየቅ ነው ተብሏል፡፡
እስካሁን በተቃዋሚ ሰልፈኞቹ እና በፖሊስ መካከል በተፈጠረ ግጭት መንግስት ባመነው 26 ሰዎች ተገድለዋል ቢባልም የመብት ተሟጋቾች እና ተቃዋሚ ፓርቲዎች ግን ቁጥሩን 40 ያደርሱታል፡፡
ትርጉም በመንገሻ ዓለሙ