የሶማሊያው የኢንፎርሜሽን ሚኒስትር ስልጣን በቃኝ አሉ፡፡
የኢንፎርሜሽን ሚንስትሩ ዳሂር ሞሀመድ ጊሌ ሀላፊነታቸውን በፈቃዳቸው የለቀቁት ፕሬዝዳንት ሞሀመድ ፋርማጆ በሚመሩት የፌደራል አስተዳደር የሀሳብ ልዩነት ስላላቸው ነው ተብሏል፡፡
አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው የሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ የጊሌ የመልቀቂያ ደብዳቤ እንደደረሰው እና ጥያቄቸውን መቀበሉን ማረጋገጫ ሰጥቷል፡፡
ዳሂር ሞሀመድ ጊሌ ከ11 ወራት በፊት በጠቅላይ ሚኒስትር አሊ ሀሰን ካይር ነበር የሶማሊያ የኢንፎርሜሽን ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት፡፡
የጊሌን ከሀላፊነታቸው መልቀቅ ተከትሎ የንግድ ሚኒስትሩ አብዲ ሃይር ማሪየ በቦታቸው የተተኩ ሲሆን የሳቸውን ቦታ ደግሞ አብዱላሂ አሊ ሀሰን እንዲይዙት ተደርጓል፡፡
መንገሻ ዓለሙ