loading
የቀድሞ የመንግስት ፋይናንስ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ዶ/ር እዮብ ተስፋዬ የኢትየጵያ ንግድ ባንክ የቦርድ ዳይሬክተር ሆነው ተሾሙ

አርትስ 18/04/2011

የኢትዮጵያን የፋይናንስ ዘርፍ በቅርበት የሚያውቁት ዶክተር እዮብ ከዘጠኙ የቦርድ ዳይሬክተሮች አንደኛው የቦርድ ዳይሬክተር ሆነውመሾማቸው ተሰምቷል
ዶክተር እዮብ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቦርድ ዳይሬከተር ሆነው መሾማቸው በኢትዮጵያ የታመመውን የፋይናንስ ዘርፍ ግልፅና ተጠያቂነትእንዲኖር፣ ችግሮቹን እና መፍትሄዎቹንም በመለየት ሊያግዝ እንደሚችል ተነግሯል፡፡

ዶ/ር እዮብን ጨምሮ ከዘጠኙ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቦርድ ዳይሬክተሮች መካከል የጠቅላይ ሚኒስትሩ ልዩ አማካሪ እና በቢሮው ዋናየንግድ ልዩ አደራዳሪ አቶ ማሞ ምህረቱ፣ በፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ የስራ ሀላፊ አቶ በየነ ገ/መስቀል፣ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮደምቱ ሀምቢሳ፣ አቶ ገመቹ ዱቢሶ፣ የዋና ኦዲተር ጀነራል እና ሌሎችም እንደሚገኙበት ከታማኝ ምንጫችን ሰምተናል፡፡

ዶ/ር እዮብ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቦርድ ዳይሬክተር ሆነው መሾማቸው፣ ከዚህ ቀደም የብሔራዊ ባንክ ለንግድ ባንኩ በቀጥታ ትዕዛዝለዚህ ድርጅት ይሄን ያህል ገንዘብ ልቀቁ፣ ለዚህም ኩባንያ ይሄን ያህል ስጡ የሚል መመሪያ ሊኖር እንደማይችል እና የብሔራዊ ባንክምከንግድ ባንኩ ጋር የሚነጋገርበት ሰፊ መንገድ ሊኖር እንደሚችል ተገምቷል፡፡

ዶ/ር እዮብ ተስፋዬ በፋይናንሱ ዘርፍ ከዚህ ቀደም ይሰሩበት ከነበረው የመንግስት ፋይናንስ ኤጀንሲ ሲሰጡዋቸው በነበሩ ማስጠንቀቂያዎችናበወቅቱ አለመደማመጥ ምክንያት ሳይግባቡ እንደቀሩ ይታወቃል፡፡

ዘገባው የሸገር  ነው

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *