loading
የቀድሞ የኢፌድሪ ኤታማጆር ሹም ጀነራል ሰዓረ መኮንን የተሰዉበት አንደኛ አመት መታሰቢያ መርሀግብር ተከናወነ።

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2012 የቀድሞ የኢፌድሪ ኤታማጆር ሹም ጀነራል ሰዓረ መኮንን የተሰዉበት አንደኛ አመት መታሰቢያ መርሀግብር ተከናወነ።በመርሀግብሩ ላይ ኢ/ር ታከለ ኡማ እና የአዲስአበባ ብልጽግና ፓርቲ ሃላፊ አቶ ተስፋዬ በልጅጌ ተገኝተዋል።ጀነራል ሰዓረ ባለፈው አመት ህይወታቸው ከማለፉ ከሰዓታት በፊት ከኢ/ር ታከለ ኡማ ጋር በመሆን ከሩዋንዳ ወደ አትላስ በሚወስደው መንገድ ላይ ችግኝ በጋራ ተክለዋል።የመታሰቢያ መርሀግብሩ እየተከናወነ ያለውም በዚህ ቦታ ላይ ነው።የከተማ አስተዳደሩ ጀነራል ሰዓረ ህይወታቸው ሲያልፍ ቦታው ላይ ፓርክ ለማሰራት ይፋ ባደረገው መሰረት የመታሰቢያ ፓርክ ግንባታው በይፋ ተጀምሯል።ከሩዋንዳ ወደ አትላስ የሚወስደው መንገድም በጀነራል ሰዓረ መኮንን ስም ተሰይሟል። በመታሰቢያ መርሀግብሩ ላይ የጀነራል ሰዓረ ቤተሰቦችና ወዳጆች እንዲሁም የተለያዩ አመራሮች ተገኝተዋል።

ምንጭ፤- ከንቲባ ጽ/ቤት

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *