loading
የተለያዩ የጦር መሳሪያ ጥይቶች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የተለያዩ የጦር መሳሪያ ጥይቶች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አርትስ 19/04/2011

በህገ-ወጥ መንገድ ወደ መሀል አገር ሊገባ የነበረ የጦር መሳሪያ ጥይት መተማ ላይ ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ መሰረት በፌደራል ፖሊስ መያዙን በጉምሩክ ኮሚሽን የባህርዳር ቅ/ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡

ግምታዊ ዋጋዉ 306 ሺ 640 ብር የሆነ 4ሺ492 የሽጉጥ እና 370 የብሬን ጥይት ትላንት ሳር በጫነ ካሮ (ጋሪ) ተደብቆ በመተማ በኩል ወደ መሀል አገር ሊገባ ሲል በፌደራል ፖሊስ በተደረገ የቁጥጥር ስራ የተያዘ ሲሆን በህገ ወጥ ስራው ተሳታፊ የነበሩ ግለሰቦችንም ይዞ ለፍርድ የማቅረብ ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉን የቅ/ጽ/ቤቱ የጉምሩክ ህግ ተገዥነት ም/ስራ አስኪያጅ አቶ አላዩ ኩርፋ ገልጸዋል፡፡

ኮንትባንድ በፖለቲካዊ፤ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ዘርፍ ላይ የሚያደርሰው አሉታዊ ተጽዕኖ ከፍተኛ በመሆኑ ቅ/ጽ/ቤቱ ኮንትሮባንድን ለመከላከል ከመቼውም ጊዜ በላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ሲሆን ህብርተሰቡም ህገ-ወጦችን በመጠቆም እና በማጋለጡ በኩል እንደወትሮው ሁሉ ሊተባበር ይገባል በማለት አሳስበዋል፡፡

ምንጭ ገቢዎች ሚኒስቴር

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *