loading
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በ38 ሀገሮች ተግባር አፍሬያለሁ አለ

አርትስ 2/1/2011
የድርጅቱ ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ የተቋሙን አመታዊ ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት እንዳሉት ሩሲያ እና ቻይናን ጨምሮ 38 የሚሆኑ ሀገሮች በዜጎቻቸው ላይ የከፋ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ያደርሳሉ፡፡
ሮይተርስ እንደዘገበው ሀገሮቹ ይፈጽሟቸዋል ከተባሉት የመብት ጥሰቶች መካከል ሰዎችን ባልሰሩት ወንጀል መክሰስ፣ ከህብረተሰቡ እንዲገለሉ መቀስቀስ፣ ግላዊ ህይዎታቸውን መሰለል የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡
ድርጅቱ በዜጎቻቸው ላይ ግፍ የሚሰሩ ብሎ ከዘረዘራቸው ሀገራት መካከል ከአፍሪካ እንደ ሀገር እውቅና ካገኘች ጀምሮ ብጥብጥ ያልተለያት ደቡብ ሱዳንን ጨምሮ ጂቡቲ፣ ግብጽ፣ ካሜሮን፣ ሩዋንዳ፣ ሞሮኮ፣ ማሊ፣ እና ዲሞክራቲክ ኮንጎ ተካተዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *