loading
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሊቢያ ተቀናቃኝ ሀይሎች ቅድሚያ ለሀገር ሰጥተው እንዲስማሙ ጠየቀ::

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2013 የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሊቢያ ተቀናቃኝ ሀይሎች ቅድሚያ ለሀገር ሰጥተው እንዲስማሙ ጠየቀ:: ድርጅቱ በሁለት ጎራ ተከፍለው ጦርነት ውስጥ የገቡት ወገኖች ከራሳቸው ይልቅ ቅድሚያ ለሀገራቸውና ለህዝቡ በመስጠት እርቀ ሰላም እንዲያወርዱ ነው ያሳሰበው፡፡ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሊቢያ ተጠባባቂ ልዩ ልኡክ ስቴፋኒ ዊሊያምስ በድርድሩ ወቅት ከራስ የፖለቲካ አከንዳ ይልቅ የሀገሩን ጉዳይ የሚያስቀድም ተወያይ እንጠብቃለን ብለዋል፡፡

ሁለቱ ተፋላሚ ሀይሎች በሚቀጥለው ኦክቶበር 26 ቱኒዚያ ላይ ውይይት እንደሚያደርጉ የተገለፀ ሲሆን በድርድሩ የውጨጭ ጣልቃ ገብነት እንዳይኖር የሚል ማሳሰቢያም ተነስቷል፡፡ ውይይቱ የተሳካ እንዲሆን ከተለያዩ ሀገራትና ተቋማት የትውጣጡ አደራዳሪዎች የሚሳተፉ ሲሆን አብዛኛዎቹ አደራዳሪዎች በመንግስታቱ ድርጅቱ የሚመረጡ ይሆናል ተብሏል፡፡

በድርጅቱ አነሳሽነት በመስከረም ወር ወደ ድርድር የገቡት የጄኔራል ከሊፋ ሀፍታር ጦርና የትሪፖሊ መንግስት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ወደ ሰከላም ሀሳብ የመምጣት አዝማሚያ እያሳዩ መሆናቸው አበረታች ጅምር ነው ተብሎናቸዋል፡፡ ጄኔራል ከሊፋ ሀፍታር ዓለም አቀፍ እውቅና ያለውን የትፖሊን መንግስት ለመጣል ነፍጥ አንግበው ጦርነት ከጀመሩ ወዲህ በርካታ ሊቢያዊያን ለሞትና ለስደት ተዳርገዋል፡፡ ዘገባው የአፍሪካ ኒውስ ነው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *