የቱርክ ባለሃብቶች በትግራይ ክልል የኢንዱስትሪ ፓርክ ሊገነቡ ነው
አርትስ 21/02/2011
የቱርክ ባለሃብቶች በትግራይ ክልል ደቡባዊ ዞን አደ ጉደም ከተማ በ750 ሚሊየን ዩሮ ስለሚገነቡት የኢንዱስትሪ ፓርክ ከከተማ አስተዳደሩናከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡
የኢንዱስትሪ ፓርኩ ግንባታ በመጭው መጋቢት ወር እንደሚጀመር እና በሁለት ዓመታት ውስጥ ተጠናቆ ወደ ስራ እንደሚገባ ነው የተነገረው፡፡
የሕንጣሎ ዋጀራት ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ከለሌ ሓጋዜ ኢንዱስትሪ ፓርኩ ተገንብቶ አገልግሎት መስጠት እንዲችል የመሬት ርክክብና ሌሎችአስፈላጊ ነገሮችን ለሟሟላት መዘጋጀታቸውን ገልፀዋል።
ፓርኩ በ500 ሄክታር መሬት ላይ የሚያርፍ ሲሆን፥ ወደ ስራ ሲገባ በዓለም ተወዳዳሪና አዲስ ቴክኖሎጂ እንደሚጠቀም ነው የሚጠበቀው፡፡
ከዚህ ባለፈም ፓርኩ የሚገነባበት አካባቢ ለመቐለ ከተማ ያለው ቅርበት የቱርክ ባለሀብቶች መዋዕለ ንዋያቸውን ለማፍሰስ እንዲመርጡት እንዳደረገው ነው አስተዳደሪው የገለጹት ።