የትግራይ ምክር ቤት የ9 የካቢኔ እና የ3 የዞን ዋና አስተዳደር ሹመት አፀደቀ
አርትስ 13/02/2011
ለ3 ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የቆየው የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት 13ኛ መደበኛ ጉባኤ 9 የካቢኔ እና 3 የዞን አስተዳደር ሹመት በማፅደቅ ተጠናቋል፡፡
ምከር ቤቱ የቀድሞዋን አፈጉባኤ አሰናብቶ አቶ ሩፋኤል ሽፋረ የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ እንዲሁም ወይዘሮ የምስራች ብርሃኑን ምክትል አፈ ጉባኤ ሾሟል፡፡
ምክር ቤቱ ከሾማቸዉ 9 የካቢኔ አዳዲስ አባላት 6ቱ ሴቶች ናቸው᎓᎓
የካቢኔ አባላቱ
1ኛ/ ዶክተር አብርሃም ተከስተ በምክትል ርእሰ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ ንግድ፣ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ ኃላፊ
2ኛ/ አቶ ቴዎድሮስ ገብረእግዚአብሄር የውሃ ሃብት ቢሮ ኃላፊ
3ኛ/ ወይዘሮ ሊያ ካሳ የክልሉ መንግስትና ህዝብ ግንኙነት ቢሮ ኃላፊ
4ኛ/ ወይዘሮ ገነት አረፈ የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ
5ኛ/ ወይዘሮ አሰፉ ሊላይ የገቢዎችና ልማት ባለስልጣን ኃላፊ
6ኛ/ አቶ ተኪኤ ምትኩ የጸጥታና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ
7ኛ/ ወይዘሮ አልማዝ ገብረጻድቅ የኮንስትራክሽን፣መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ
8ኛ/ ወይዘሮ ብርክቲ ገብረመድህን የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ እና
9ኛ/ ዶክተር ጸጋብርሃነ ተክሉ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ ሆነዋል።
እንዲሁም አቶ ኢያሱ ተስፋይ የማዕከላዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ፣አቶ ረዳኢ ሐለፎም የትግራይ ደቡባዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪ እና አቶ ርስኩ አለማው የምዕራብ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሆነዉ ተሹመዋል።