loading
የትግራይ ክልል ወደቀደመው መረጋጋትና ሰላም እየተመለሰ መሆኑ ተገለጸ::

አዲስ አበባ፣ ህዳር 30፣ 2013  የትግራይ ክልል ወደቀደመ ሰላሙና መረጋጋት እየተመለሰ መሆኑን የትግራይ ብልጽግና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ነብዩ ስሁልሚካኤል አስታወቁ:: በክልሉ የመማር ማስተማር ሂደቱን ለማስጀመር የትምህርት ሚኒስቴር ተጨማሪ 50 ሚሊዮን ብር መመደቡን ገለጸዋል፡፡

አቶ ነብዩ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንዳስታወቁት፤ በህወሓት ቡድን ወደ አለመረጋጋት ገብቶ የነበረው የትግራይ ክልል አሁን ላይ ወደቀደመ ሰላምና መረጋጋቱ እየተመለሰ ይገኛል:: ችግሩ ከተፈጠረበት ዕለት ጀምሮ ጉዳዩ ሀገራዊ ጉዳይ ተደርጎ ከፍተኛ ርብርብ እንደተደረገበት እንደሚገኝ ያስታወቁት አቶ ነብዩ ፣ የተገኘው ውጤት ነገሮች በጋራ ሲሰሩ ምን ያህል አመርቂ ውጤት ማግኘት እንደሚቻል ያሳየ ነው ብለዋል::

አሁን ላይ በክልሉ መደበኛ ሕይወት እየተጀመረ ነው፤ የፈረሰው አስተዳደር በጊዜያዊ አስተዳደር እየተተካ ነው ፤ ሕዝቡም እየተወያየ ይምራኝ የሚለው እና ራሱ የመረጠው አካል እንዲመራው እየተደረገ መሆኑን አመልክተዋል:: በአክሱም፣ በሽሬ ፣ በአላማጣ በአጠቃላይ ምዕራብ ትግራይና ደቡብ ትግራይ መቀሌ ጨምሮ በሌሎች አካባቢዎች ላይም ሕዝቡ እየተወያየ መሪውን እየመረጠና ወደመረጋጋት እየተመለሰ መሆኑን አብራርተዋል::አገልግሎት ሰጭ የመንግሥት ተቋማትን ወደ ስራ እየተመለሱ መሆኑንም ገልጸዋል::

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *