loading
የቶታል ካፍ ኮንፌዴሬሽን የምድብ ድልድል ይፋ ሁኗል

የቶታል ካፍ ኮንፌዴሬሽን የምድብ ድልድል ይፋ ሁኗል

የ2018/19 የቶታል ካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የምድብ ድልድል በትናንትናው ዕለት በግብፅ መዲና ካይሮ የካፍ ዋና መስሪያ ቤት ይፋ ሁኗል፡፡

በዚህም ምድብ አንድ ላይ ሶስት የሞሮኮ ቡድኖችን ያገናኘ ምድብ ሲወጣ፤ ጅማ አባ ጅፋርን ከውድድር ያሰናበተው ሃሳኒያ አጋዲር፣ ኤ.ኤስ ኦቶሆ ደ.ኦዮ (ኮንጎ)፣ ቤርካኔ (ሞሮኮ)፣ ራጃ ካዛብላንካ (ሞሮኮ)፤

ምድብ ሁለት ላይ ኢትዋል ደ ሳህል (ቱኒዚያ)፣ ሬንጀርስ ኢንተርናሽናል (ናይጄሪያ)፣ ሳሊታስ (ቡርኪና ፋሶ) እና ሲ.ኤስ ሰፋክሲያን (ቱኒዚያ) ተደልድለዋል፡፡

በምድብ ሶስት ደግሞ ዜስኮ ዩናይትድ (ዛምቢያ)፣ አል ሂላል (ሱዳን)፣ አሳንቴ ኮቶኮ (ጋና) እንዲሁም ንካና (ዛምቢያ) ተካትተዋል፡፡

በአራተኛው ምድብ ጎር ማሂያ (ኬንያ)፣ ና ሁሴን ዴይ (አልጄሪያ)፣ አትሌቲኮ ፔትሮሌስ (አንጎላ) እና ዛማሊክ (ግብፅ) በመሆን ተደልድለዋል፡፡

የምድብ ድልድሉን የካፍ ምክትል ዋና ፀሃፊ አንቶኒ ባፎ እና የካሜሮን የቀድሞ ተጫዋች ፓትሪክ ምቦማ መርተውታል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *