loading
የአለም የምግብ ፕሮግራም ለፍልስጤም ሳደርግ  የነበረውን ድጋፍ አቋርጫለሁ አለ፡፡

የአለም የምግብ ፕሮግራም ለፍልስጤም ሳደርግ  የነበረውን ድጋፍ አቋርጫለሁ አለ፡፡

ድርጅቱ እርዳታውን ያቋረጥኩት  ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለሰብዓዊ እርዳታ የሚደረገው ድጋፍ እየቀነሰ በመምጣቱ ነው ብሏል።

በፍልስጤም ለሚደረገው የሰብዓዊ እርዳታ የአንበሳውን ድርሻ ታበረክት የነበረችው አሜሪካ ነበረች፡፡

አሜሪካ ድጋፍ ማድረጓን ካቋረጠች ጀምሮ  በድርጅት የሚደረገው ዓለም አቀፍ የእርዳታ  መጠን እየቀነሰ መምጣቱን ቢቢሲ በዘገባው አስነብቧል።

በዚህ ምክንያትም ከፈረንጆቹ ጥር ወር መጀመሪያ አንስቶ 27 ሺህ የሚሆኑ ፍልስጤማውያን ከዚህ በፊት ያገኙት የነበረው እርዳታ የተቋረጠባቸው መሆኑን በፍልስጤም የድርጅቱ ዳይሬክተር ስቴቨን ኬርነይ ተናግረዋል።

በተለይም በእስራኤል ቁጥጥር ስር በሚገኙት የዌስት ባንክና ጋዛ ሰርጥ ነዋሪዎች ላይ ከዚህ በፊት ይደረግ የነበረው እርዳታ በአስከፊ ሁኔታ እየቀነሰ መምጣቱን እና በአሁኑ ሰአት ለአስቸኳይ እርዳታ የሚውል 57 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር እንደሚያስፈልግ ነው ዳይሬክተሩ የተናገሩት።

በተጠናቀቀው የፈረንጆቹ አመት የአለም የምግብ ፕሮግራም 250 ሺህ ለሚሆኑ የጋዛ ነዋሪዎችና 110 ሺህ ለሚሆኑ የዌስት ባንክ ነዋሪዎች ድጋፍ ማድረጉ ይታወሳል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *