loading
የአረንጓዴ ዐሻራ አላማ የለም አፈር መሸርሸርን ማስቀረት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ተናገሩ::

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 10 ፣ 2012  የአረንጓዴ ዐሻራ አላማ የለም አፈር መሸርሸርን ማስቀረት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ተናገሩ::ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ እንዳሰፈሩት የአረንጓዴ ዐሻራ አላማ የለም አፈር መሸርሸርን ማስቀረት መሆኑን ገልጸዋል፡፡የደን ምንጣሮ እና የአየር ንብረት ለውጥ ከሌሎች መንሥኤዎች ጋር ተዳምረው በየዓመቱ በኢትዮጵያ የለም አፈር መሸርሸርን ያስከትላሉ ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ።የአረንጓዴ ዐሻራ አንዱ ግብ ይህንን እጦት መቀልበስ መሆኑንም ጠቅሰዋል::ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በረሃማነትን እና ድርቅን ለመቀነስ የሚደረጉ ጥረቶችን በሚያከብርበት በዚህ ዕለት፤ሁላችንም በኢትዮጵያ የአረንጓዴ ዐሻራ እንቅስቃሴ እንሳተፉ ሲሉ ጥሪ አቀርበዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *