loading
የአራተኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ዛሬና ነገ ቀጥለው ይካሄዳሉ
አርትስ ስፖርት 22/03/2011
በተለያዩ ምክንያቶች እየተቆራረጠ የሚካሄደው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ፤ በ4ኛ ሳምንቱ ዛሬና በነገው ዕለት በአዲስ አበባ እና ክልል ስታዲየሞች ግጥሚያዎች ይከናወናል፡፡
በዚህም ዛሬ በትግራይ ስታዲየም እስካሁን በሊጉ በሁለት ጨዋታዎች ጉዞ ምንም ነጥብ ማግኘት ያልቻለው ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በ9፡00 ሰዓት ደቡብ ፖሊስን ያስተናግዳል፡፡
እሁድ ደግሞ አምስት ያህል ጨዋታዎች ክልል እና አዲስ አበበባ ላይ  ሲከናወኑ በፋሲለደስ ስታዲየም ፋሲል ከነማ ከኢትዮጵያ ቡና ይጫወታሉ፤ ኢንተርናሽናል ዳኛ በላይ ታደሰ ጨዋታውን ይመሩታል፡፡
ሶዶ ላይ ወላይታ ድቻ ከሊጉ መሪ መቐለ 70 እንደርታ ጋር የሚፋለም ሲሆን ባህር ዳር ከነማ በባህር ዳር ስታዲየም ከ ሀዋሳ ከነማ ጋር ግጥሚያቸውን ያከናውናሉ፡፡ አርቢትር ኢያሱ ፈንቴ በሚመሩት ጨዋታ ደግሞ አዳማ ከተማ ከሲዳማ ቡና በአዳማ አበበ ቢቂላ ስታዲየም ላይ ይገናኛሉ፡፡
ክልል ላይ የሚከናወኑት ሁሉም ጨዋታዎች በተመሳሳይ 9፡00 ሰዓት ይካሄዳሉ፡፡
በ10፡00 በአዲስ አበባ ስታዲየም ቅዱስ ጊዮርጊስ ስሑል ሽረ ጋር ይጫወታሉ፤ ጨዋታውን አርቢትር ብርሃኑ መኩሪያ ይመሩታል ተብሏል፡፡
ሊጉን መቐለ 70 እንደርታ፣ ኢትዮጵያ ቡና እና ሀዋሳ ከነማ በእኩል ስድስት ነጥብ በግብ ክፍያ ተበላልጠው ሲመሩት ሲዳማ ቡና እና ባህር ዳር ከነማ በአራት ነጥብ ይከተላሉ፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *