የአንጎላ ፖሊሶች የኮሮና ቫይረስ ገደብን በተላለፉ ሰዎች ላይ በወሰዱት እርምጃ የ7ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡
አዲስ አበባ፣ነሐሴ 20፣ 2012 የአንጎላ ፖሊሶች የኮሮና ቫይረስ ገደብን በተላለፉ ሰዎች ላይ በወሰዱት እርምጃ የ7ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡ፖሊሶች በተጠቀሙት ያልተገባ ሀይል ከሞቱት ዉስጥ ወጣቶችና አፍላ እድሜ ላይ የነበሩ ታዳጊዎችም ይገኑበታል፡፡ ለኮሮና ቫይረስ የተቀመጠዉን ገደብ ተላለፈዉ በመገኘታቸዉ በፖሊስ ተተኩሶባቸዉ መገደላቸዉ ነዉ የተሰማዉ ፡፡
ድርጊቱን በተመለከተ የዓለም አቀፍ መብት ተማጓቹ አሚኒስቲ ኢንተርናሽናል በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ ሰዎች እንዳይሞቱ የዓለም መንግስታት እየታገሉ ባሉበት ለማስጠንቀቅ ተብሎ የወጣዉን መመሪያ ተገን አድርጎ መግደል ተቀባይነት የሌለዉ ነዉ በማለት ተቃዉሞታል ሲል ነዉ አልጀዚራ የዘገበዉ ፡፡
በአንጎላ ያለዉ የብሪታያ የጥበቃ ብድን ኦማኒጋር ከተሰኘዉ የአንጎላ የመብት ተማጓቾች ጋር ባደረኩት ምርመራ አብዛኞቹ ተጎጂዎች በፖሊስና በሰራዊት መኮንኖች እንደተገደሉና ወጣቶች ተሰባስበዉ ስፖርት እየሰሩ ባለበት ሁኔታ ላይ ፖሊሶች እንዲበተኑ በማሰብ በተኮሱት ተኩስ ባሉበት መሞታቸዉ ነዉ ደርሼበታለሁ ሲል አስታዉቋል፡፡
የሀገሪቱ መንግስት የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት በሚል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማዉጣት ከመጋቢት ወር ጀምሮ ገደቦች የጣለ መሆኑንና መመሪያዉን ለማስፈፀም የፀጥታ አስከባሪዎች ተሰማርተዉ እንደነበርም ይታወሳል፡፡የፀጥታ አስከባሪዎች በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ ከመመሪያዉና ከህግ ዉጪ ሀይል እንዳይጠቀሙ ለማድረግ እንዲቻል የሀገሪቱ መንግስት የሰብዓዊ መብት እንዲከበር አስቸኳይ እርምጃ መዉሰድ አለበት ሲሉ በሀገሪቱ የሚገኘዉ ኦማኒጋር የተሰኘዉ የመብት ተሟጋች አሳስቧል ፡፡