loading
የአውስትራሊያው ጠቅላይ ሚንስትር ስኮት ሞሪሰን የምርጫ ቅስቀሳ ሲያደርጉ በእንቁላል ተመቱ፡፡

የአውስትራሊያው ጠቅላይ ሚንስትር ስኮት ሞሪሰን የምርጫ ቅስቀሳ ሲያደርጉ በእንቁላል ተመቱ፡፡

ቢቢሲ እንደዘገበዉ ጠቅላይ ሚንስትሩ ከሀገሪቱ ምርጫ አስቀድመው ቅስቀሳ ሲያደርጉ ነበር በእንቁላል ከበስተጀርባ ጭንቅላታቸዉን የተመቱት።

የእንቁላል ዉርወራዉን ተከትሎም አንዲት የ25 ዓመት ሴት በቁጥጥር ስር መዋሏ የተሰማ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ድርጊቱን አሳፋሪ ነዉ በማለት ጠባቂዎቻቸው ነገሩን በፍጥነት በቁጥጥር ስር በማዋላቸው አመስግነዋቸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን በሀገሪቱ የሴቶች ማኅበር ውስጥ ቅስቀሳ በሚያደርጉበት ወቅት ነበር በእንቁላል የተመቱት።

በቦታው ሌላ ምንም ጉዳት አለመድረሱን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሀን የዘገቡት ሲሆን፤ እንቁላሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጭንቅላት ላይ ካረፈ በኋላ ሳይሰበር ከመሬት አርፏልም ብለዋል።

ስኮት ሞሪሰን በዚህ ዓመት በእንቁላል የተመቱ ብቸኛው አውስትራሊያዊ ፖለቲከኛ አይደሉም።

ፍራስተር አኒንንግ የተባሉ ፖለቲከኛ በኒውዝላንድ መስጊድ ውስጥ ስለደረሰው ጥቃት አወዛጋቢ አስተያየት መስጠታቸውን ተከትሎ እንቁላል ተወርውሮባቸው ነበር።

የአውስትራሊያ ሀገር አቀፍ ምርጫ ከሰባት ቀን በኋላ ይካሄዳል።

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *