የአዲስ አበባ ምርጫ ለምን ዘግይቶ ይካሄዳል ?
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2013 6ተኛ ሀገር አቀፍ ምርጫ ግንቦት 28 2013 ዓ.ም እንደሚካሄድ የተገለጸ ሲሆን የአዲሰ አበባ ከተማ አሰተዳደር ምርጫ ደግሞ ሰኔ 5 መካሄዱ ጥያቄ ማስነሳቱ ይታወቃል፡፡ ይህንን የመራጮች ድምጽ መስጫ ቀን ልዩነትን በተመለከተ አርትስ ቴሌቭዥን ምርጫ ቦርድን ጠይቋል፡፡
የከተማ መስተዳድሮች እና ክልሎች የምርጫ ክልሎቻቸውን የመወሰን ስልጣን የከተማ መስተዳድሮች እና የክልሎች በመሆኑ የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ከ 2ሺህ ዓ.ም ጀምሮ የምርጫ ክልሌን ማቋቋም የምፈልገው በምክር ቤቱ መቀመጫ ሳይሆን በክፍለ ከተሞቼ ነው በማለቱ ከፌደራል ምርጫ ክልል ጋር የተለያየ ለመሆን መቻሉን የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የሆኑት ሶሊያና ሽመልስ ተናግረዋል፡፡
የአዲስ አበባ ምርጫ ዘግየቶ መካሄድ በብዙዎች ዘንድ ጥያቄን እየፈጠረ ያለ ውሳኔ መሆኑን ያነሱት ሶሊያና፤ ምርጫውን አንድ ላይ ማድረግ የሚቻል ቢሆንም ብዙ ተወዳዳሪዎች እና መራጮች የሚኖሩበት አካባቢ ከመሆኑ አንፃር የድምፅ አሰጣጡ እና ቆጠራው በስርዓት ለማስኬድ አስቸጋሪ እንደሚሆን ገልፀዋል፡፡
የምርጫው አንድ ላይ ለማስኬድ አድካሚና ብዙ ፈሰስ የሚጠይቅ መሆኑን ለአርትስ በሰጡት ቃለ-ምልልስ ተናግረዋል፡፡