የአዲስ አበባ ስታድየም በዛሬው ዕለት በአፍሪካ የመጀመርያዉ የአየር ብክለት መለኪያ ተገጠመለት
አርትስ ስፖርት 23/02/201
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን እንዳስታወቀዉ የአየር በክለት መለኪያ መሳሪያዉ በአለም አቀፍ ደረጃ በአሁኑ ሰዓት በፈረንሳይ – ሞናኮና፤ በአርጀንቲና – ቦነስ አይረስ ብቻ የሚገኝ ነው ።
ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ ከአለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር ፣ የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት አትሌት ኃይሌ ገ/ስላሴ እና ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴአባላት በተገኙበት መሳሪያውን በይፋ ስራ ጀምሯል፡፡
የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት አትሌት ኃይሌ ፥ ኢትዮጵያን ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት በተለየ መርጦ በኢትዮጵያ የአየር ብክለት መለኪያ እንዲገጠም በማድረጉምስጋና ያቀረበ ሲሆን፤ ይህ መሣሪያ ለሀገሪቱ የአትሌቲክስ እንቅስቃሴ የጎላ ጠቀሜታ እንደሚኖረው ተነግሯል፡፡