የአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር ያለግንባታ ለረዥም ግዜ ታጥረዉ የቆዩ ቦታዎችን ማፍረስ ጀመረ
አርትስ 10/03/2011
አስተዳደሩ የህብረተሰቡን የልማት ጥያቄ ለመመለስ በቅርቡ የህዝብና የመንግስት ውስን ሃብት የሆነውን መሬት ለበርካታ ዓመታት ያለልማት አጥረው ይዘው በቆዩ ባለሀብቶች ላይ እርምጃ መውሰዱይታወቃል፡፡ እነዚህ አካላት አጥረው ካስቀመጡት ቦታዎች ላይ ንብረቶቻቸውን እንዲያነሱ ከአንድ ሳምንት በፊት መግለጫ ቢሠጥም ንብረቶቻቸውን ሊያነሱ አልፈቀዱም ብሏል አስተዳደሩ በመግለጫዉ፡፡
የከተማ አስተዳደር ህግና ሥርዓትን የማስከበር ኃላፊነት ስላለበት በዛሬው ዕለት የአዲስ አበባ መሬት ልማት ማኔጅመንት ፅ/ቤት የደንብ ማስከበር ፅ/ቤት እንዲሁም የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በጋራበመሆን የአጥር ቆርቆሮዎችን ማንሳት ጀምረዋል፡፡
አስተዳደሩ በዚህ አጋጣሚ የህዝብን ሃብት ለተገቢው ልማትና የነዋሪዎች ተጠቃሚነት እንዲውል በጀመራቸው ተግባራት፤ ህገ-ወጥነትን በየትኛውም መንገድ እንደማይታገስና፤ ህግ የማስከበር ሃላፊነቱንእንደሚወጣ ያረጋግጣል ብሏል፡፡