የአድዋን ታሪክ በሚገባ በመለየት አሁን ላለንበት ችግር መፍቻ ቁልፍ ማድረግ ይገባል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህል ኪነ ጥበባትና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ሂሩት ካሳው ገለጹ።
አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2014 የአድዋን ታሪክ በሚገባ በመለየት አሁን ላለንበት ችግር መፍቻ ቁልፍ ማድረግ ይገባል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህል ኪነ ጥበባትና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ሂሩት ካሳው ገለጹ። ለ126ኛ ጊዜ “አድዋን ለኢትዮጵያውያን ኅብረት፣ ለአፍሪካ የነፃነት ጮራ” በሚል መሪ ሃሳብ የሚከበረውን የአድዋ ድል በዓል አስመልክቶ የውይይት መድረክ ተካሄዷል፡፡
የቢሮ ኃላፊዋ በመድረኩ ላይ እንደገለጹት፣ አድዋ የነጻነት ድል ብቻ ሳይሆን ፍትህ፣ አርነት እና ሉአላዊነት የተገኘበት ነው፤ ይህን በተለየ መንገድ ማየትና መጠቀም ያስፈልጋል። የአድዋ ድል ኢትዮጵያ ለአለም ፍትህን ያሳየችበትና በአለም እይታ ውስጥ የገባችበት ድል ነው ፤ ስለዚህ አድዋን በሚገባ በመረዳት አሁን ላለንበት ችግር የመፍቻ ቁልፍ አድርጐ መጠቀም ያስፈልጋል ብለዋል። በፓናል ውይይቱ ከአድዋ ምን መማር አለብን፤ ከአድዋ በኋላ ኢትዮጵያ ምን አገኘች፣ ምን ሆነች፣
በሚሉ ጉዳዮች ዙሪያ ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት እየተደረገባቸው ነው። በውይይቱ አባትና እናት አርበኞች፣ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተወካዮችና ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት መገኘታቸው ታውቋል፡፡