የአፍሪካ ህብረት የሱዳን ወታደራዊ ምክር ቤት ስልጣን የሚያስረክብበትን ቀነ ገደብ አራዘመ፡፡
የአፍሪካ ህብረት የሱዳን ወታደራዊ ምክር ቤት ስልጣን የሚያስረክብበትን ቀነ ገደብ አራዘመ፡፡
የአፍሪካ መሪዎች በሱዳን እና በሊቢያ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለመምከር ካይሮ ላይ በተገናኙበት ወቅት ነው ውሳኔው የተላለፈው፡፡
ህብረቱ ቀደም ሲል ባወጣው መግለጫ ወታደራዊ ምክር ቤቱ በ15 ቀናት ውስጥ ስልጣኑን ለሲቪል የሽግግር መንግስት እንዲያስረክብ ይህ ባይሆን ግን ሱዳን ከህብረቱ እንደምትባረር አስጠንቅቆ ነበር፡፡
የግብፁ የዜና ወኪል ሜና እንደዘገበው በካይሮው አስቸኳይ ስብሰባ የተሳተፉት የአፍሪካ መሪዎች እና ተወካዮች ተመካክረው ለ15 ቀናት የተሰጠው ቀነ ገደብ ወደ 3 ወር እንዲራዘም ወስነዋል፡፡
የአፍሪካ ህብረትን በሊቀ መንበርነት የሚመሩት ፕሬዝዳንት አብደልፈታህ አልሲሲ ቃል አቀባይ ባሳም ራዲ እንዳሉት የ3 ወር ጊዜ መስጠት ያስፈለገው መጀመሪያ የተሰጠው ጊዜ በቂ አለመሆኑ ስለታመነበት ነው፡፡
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋቂ ማሃማትን ጨምሮ ከኢትዮጵያ እና ከሌሎች በርካታ የአፍሪካ ሀገራት የተወከሉ ልኡካን በስብሰባው ተሳትፈዋል፡፡
መንገሻ ዓለሙ