loading
የኢትዮ-ሩስያ የስነ-ህይወታዊ አካላት የምርምር ማዕከል በኢትዮጵያ ሊቋቋም ነው፡፡

የኢትዮ-ሩስያ የስነ-ህይወታዊ አካላት የምርምር ማዕከል በኢትዮጵያ ሊቋቋም ነው፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስት ዶ/ር  ኢንጂ ጌታሁን መኩሪያ አዲስ ከተሾሙት በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢቭጀኒ ተረኪህን ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡
ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ እና የሩስያ መንግስታት የጋራ ኮሚሽን የኢትዮጵያ በኩል ሰብሳቢ በመሆናቸው የጋራ ኮሚሽኑ ስብሰባ በሚካሄድበት ቀንና በሚቀርቡ አጀንዳዎች ዙርያ ተነጋግረዋል፡፡
የኒውክሌር ቴክኖሎጂን ለህክምናና ለሃይል መጠቀም እንዲቻል በተቀመጠው ፍኖታ ካርታ ትግበራ ዙርያም መክረዋል፡፡
የሩስያ የሳይንስ አካዳሚ ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የኢትዮ-ሩስያ የስነ-ህይወታዊ አካላት የምርምር ማዕከል ለማቋቋም እቅድ ተይዟል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ተነጋግረው በሚያስቀምጡት አቅጣጫ መሰረት ወደ ትግበራ ይገባል፡፡
ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እንዳገኘነዉ መረጃ  የሩስያ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ በማዕድን ፍለጋ መስክ ( በወርቅና ታንታለም) መሰማራት በሚችሉበት መንግድ ላይም  ተወያተዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *