የኢፌዴሪ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳን የቀብር ስነ ስርዓት የሚያስፈፅም ብሄራዊ ኮሚቴ ተቋቁሞ ወደ ስራ መግባቱ ተገለፀ
የኢፌዴሪ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳን የቀብር ስነ ስርዓት የሚያስፈፅም ብሄራዊ ኮሚቴ ተቋቁሞ ወደ ስራ መግባቱ ተገለፀ
የብሄራዊ ኮሚቴው ከፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት፣ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት፣ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከመከላከያ ሚኒስቴር፣ ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን እና ከቤተሰቦቻቸው በመውጣት የተዋቀረ መሆኑም ተነግሯል።
የብሄራዊ ኮሚቴውም በገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር እዮብ ተካልኝ የሚመራ መሆኑም ተገልጿል።
የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር እዮብ ተካልኝ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያና የቀብር ስነ ስርዓት የሚያስፈፅም ብሄራዊ ኮሚቴ አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም የቀብር ስነ ስርዓቱን የሚስፈጽመው ብሄራዊ ኮሚቴው በስሩ 3 ንዑስ ኮሚቴዎችን ያሉት መሆኑን ገልፀዋል።
ንዑስ ኮሚቴዎቹም የቀብር ስነ ስርዓት፣ የደህንነትና ጥበቃ እንዲሁም የሎጂስቲክስ ጉዳዮችን የሚያሳልጡ ሲሆን፥ የቤተሰብ አባላትም ተካተውበታል ነው ያሉት።
አስከሬናቸው አስካሁን ሆስፒታል እንዳለ የገለፁ ሲሆን፥ ሆስፒታሉ ምርምራ ጨርሶ መልቀቂያ እንደሰጠ ወደ ሀገር ቤት ሲገባ አቀባበል ለማድርግ እየተጠበቀ ነው መሆኑንም ኮሚቴው አስታውቋል።
የቀድሞ ፕሬዝዳንት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ አስክሬን ወደ ሃገሩ የሚገባበት ቀን አይታወቅም ያለው ኮሚቴው፥ አሁን ባለው መረጃ ግን በዚህ ሳምንት መጨረሻ ሊሆን እንደሚችል አመልክቷል።
ቀኑ ሲረጋገጥ የቀብር ስነ ስርዓቱን የተመለከተ ብሄራዊ ኮሚቴው መረጃ የሚያወጣ መሆኑን ፋና ዘግቧል፡፡