የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በእንስት ዋና ስራ አስፈፃሚ ሊመራ ነው
አርትስ ስፖርት 05/03/2011
ተወዳጁ የእንግዝ ፕሪምየር ሊግ አዲስ ዋና ስራ አስፈፃሚ ያገኘ ሲሆን አዲሷ ኃላፊ ደግሞ ሱዛና ዲኔጅ ይሰኛሉ፤ ሪቻርድ ስኩዳሞርን በመተካትም በቅርቡ አዲሱን ኃላፊነት ይረከባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ዲኔጅ ፕርሚየር ሊጉን የተቀላቀሉት ከ media organisation Discovery ከተሰኘ የመገናኛ ብዙሀን ተቋም Animal Planet channel ፕሬዚዳንትነት ተነስተው ነው፡፡
የ59 ዓመቱ ዋና ስራ አስፈፃሚ ስኩዳሞር ከ19 ዓመት የኃላፊነት ቆይታ በኋላ በሚቀጥለው ወር ይሰናበታሉ፡፡ ዲኔጅም ፕሪምየር ሊጉን በመመምራት ከ ሪክ ፔሪ እና ሪቻርድ ስኩዳሞር በመቀጠል ሶስተኛዋ ግለሰብ ይሆናሉ፡፡
‹‹ይህን ቅዥት የሆነ ኃላፊነት በመረከቤ በጣም ተደስቻለሁ፤ ፕሪምየር ሊጉ ማለት እኮ ለብዙ ሰዎች ከምንም በላይ ነው›› ሲሉ ዲኔጅ ተናግረዋል፡፡
‹‹የፕሮፌሽናል ስፖርት የመጨረሻ ጫፍ የሚወከልበት ነው፤ ይህንንም በጣም ተወዳጅ እና የሚያኩራራ ድርጅት ለመምራት በመታደሌ ትልቅ ክብር ይሰማኛል›› ሲሉ አክለዋል፡፡
በክለቦችና ቡድኖች እገዛም ለመጭዎቹ አመታት የሊጉን የስኬት ጉዞ ወደፊት አስቀጥላለሁ ሲሉ ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡
አዲሷ ዋና ስራ አስፈፃሚ እ.አ.አ በጥር 2009 Discovery ከመቀላቀላቸው አስቀድሞ ለ10 ዓመታት ያህል በ Channel Five የሰሩ ሲሆን የስራ ዘመናቸውን በ MTV አሀዱ ብለው ጀምረዋል፡፡
ቢቢሲ እንደዘገበዉ የፕሪምየር ሊጉ እጩ አቅራቢ ኮሚቴ ለዚህ ከፍተኛ ኃላፊነት እንዲህ ያለ የመሪነት አቅም ያላቸውን ሰው መሾም በጣም ያረካናል ብሏል፡፡