loading
የኦሮሚያ ፀረ ሙስና ኮሚሽን በክልሉ በሙስና የጠረጠራቸዉን 56 ሰዎችን በህግ ቁጥጥር ስር አዋለ

የኦሮሚያ ፀረ ሙስና ኮሚሽን በክልሉ በሙስና የጠረጠራቸዉን 56 ሰዎችን በህግ ቁጥጥር ስር አዋለ

አርትስ 15/04/2011

ኮሚሽኑ በክልሉ የተለያዩ  መስሪያቤቶች የሚገኙ በተለያየ ሙያና የስራ ሃላፊነት ላይ የሚገኙ የክልሉ ሰራተኞች ላይ ሲያደርግ የነበረውን ክትትል አጠናቆ  ነዉ 56 ቱን በህግ ቁጥጥር ስር ያዋለዉ፡፡

ተጠርጣሪዎችን ተከታትሎ በቁጥጥር ስር የማዋሉ ስራ የሚቀጥል ሲሆን፤ ሰሞኑን እየተሰራ ባለው ስራና እየተወሰደ ባለው እርምጃ፤ የኮሚሽኑ ሃላፊዎች ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ እንደሚሰጡ የኦዲፒ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የገጠር ፖለቲካና የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ በፌስቡክ ገጻቸዉ ይፋ አድርገዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *