loading
የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በይፋ ተጀመረ።

የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በይፋ ተጀመረ። መርሀግብሩ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 አርሶአደሮች መንደር ላይ ነው የተጀመረው።ኢ/ር ታከለ ኡማ ከግብርና ሚንስትሩ ዑመር ሁሴን ጋር በጋራ በመሆን መርሀግብሩን አስጀምረዋል። በዛሬው እለትም የከተማው በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች አርሶ አደሮች ማሳ ላይ በመገኘት አርሶአደሮቹን ያገዙ ሲሆን በተለያዩ አካባቢዎችም ችግኝ ተክለዋል። ኢ/ር ታከለ ኡማ የዘንድሮው የበጎ ፈቃድ መርሀግብር አዋሳኝ አካባቢ የሚገኙ ነዋሪዎችና አርሶአደሮችን ያካትታል ያሉ ሲሆን ይህም በጋራ የማደግ መንፈስን የያዘ ነው ብለዋል። በበጎ ፈቃድ ድጋፉ አርሶ አደሮቹን ከመደገፍ ባለፈ አርሶአደሮቹ የተሻለ ምርት አምርተው ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ ሊፈጠር የሚችል የምርት እጥረትን መከላከል እንዲያስችል የታለመ ነው ብለዋል ኢ/ር ታከለ። ለአርሶ አደሮቹ የምርጥ ዘር ድጋፍ ተደርጎላቸዋል። የበጎ ፈቃድ መርሀግብሩ ለአራት ወራት የሚቆይ ይሆናል።

ምንጭ፤- ከንቲባ ጽ/ቤት

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *