loading
የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አካል የሆነው የቤት እድሳት መርሀግብር በይፋ ተጀመረ::

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2012 የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አካል የሆነው የቤት እድሳት መርሀግብር በይፋ ተጀመረ::ኢ/ር ታከለ ኡማ በሚኖሩበት አካባቢ ነዋሪ የሆኑት ወ/ሮ ቀነኒ ሁንዴ መኖሪያ ቤት በመገኘት የቤት እድሳት መርሀግብሩን አስጀምረዋል :: በየአካባቢው የሚገኙ ለኑሮ አስቸጋሪ በሆነ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ አቅመደካማች መኖሪያ ቤታቸው የሚታደስ ይሆናል :: በመኖሪያ ቤት እድሳቱ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሰጪ ወጣቶችና የተለያዩ አካላት የሚሳተፉ ይሆናል ከቤት እድሳት መርሀግብር በተጨማሪም “አንድ ቤተሰብ ለአንድ ሰው” እርስ በእርስ የመደጋገፍ መርሀግብር በይፋ ይጀመራል::በመርሀግብሩ እያንዳንዱ ቤተሰብ በአቅራቢያው ላለ ሌላ የኑሮ አቅሙ ደከም ላለ ቤተሰብ ድጋፍ የሚያደርግበትና ያለውን የሚያካፍልበት ነው:: “በአንድ ቤተሰብ ለአንድ ሰው” መርሀግብር የከተማዋ ነዋሪዎች፣በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች፣ታዋቂ ግለሰቦች፣የከተማዋ ባለሀብቶችና የከተማዋ አመራሮች ይሳተፋሉ::

ምንጭ፤-የከንቲባ ጽ/ቤት ነዉ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *