የኮንጎው ተቃዋሚ ፓርቲ እጩ ተወዳዳሪ በምርጫ ማግስት በኮቪድ-19 ምክንያት ህይዎታቸው ማለፉ ተሰማ::
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 13 ፣ 2013 የኮንጎው ተቃዋሚ ፓርቲ እጩ ተወዳዳሪ በምርጫ ማግስት በኮቪድ-19 ምክንያት ህይዎታቸው ማለፉ ተሰማ::
የተቃዋሚ ፓርቲን ወክለው በእጩነት ቀርበው የነበሩት ብሪስ ፓርፋይት ለላስ በምርጫው ዋዜማ እለት ነበር በቫይረሱ መያዛቸው በመረጋገጡ ሆስፒታል የገቡት፡፡ኮለላስ ህመማቸው ሲበረታ የተሻለ ህክምና እንዲደረግላቸው ወደ ፈረንሳይ ተወስደው እንደነበርም የምርጫ ቅስቀሳ ዳይሬክተራቸው ተናግረዋል፡፡
ይሁን እንጂ እጩ ተወዳዳሪው ገና በአውሮፕላ ጉዞ ላይ እንዳሉ ህይዎታቸው ማለፉን አልጀዚራ በዘገባው አስነብቧል፡፡
ኮለላስ ገና በሽታው እያዳከማቸው ሲመጣ በሆስፒታል አልጋ ላይ ሆነው ባስተላለፉት መልአክት እኔ ከሞት ጋር እየታገልኩ ነው ፤ውድ የሀገሬ ሰዎች በምርጫው በንቃት ተሳትፋቸው ለውጥ አምጡ ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ ህመሙ ሲጀምራቸው በወባ እንደተያዙ ግምት እንደነበራቸው ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ተናግረው ነበር፡፡
ኮለላስ ሞት በይቀድማቸው ኖሮ በምርጫው ሀገሪቱን ለ24 ዓመታት የመሯት ዴኒስ ንጉዌሶ ብርቱ ተፎካካሪ ሆነው ቀርበው እንደነበር ተነግሯል፡፡
የምርጫው ውጤት ገና ይፋ ባይሆንም ፕሬዚዳንት ንጉዌሶ ዳግም እንደሚያሸንፉ ከወዲሁ ግመቶች ተበራከተዋል፡፡