የኮንጎው ፕሬዝዳንት የመጀመሪያ የውጭ ሀገር ጉብኝታቸውን ሊያደርጉ ነው፡፡
የኮንጎው ፕሬዝዳንት የመጀመሪያ የውጭ ሀገር ጉብኝታቸውን ሊያደርጉ ነው፡፡
በአወዛጋቢ የምርጫ ውጤት ወደ ስልጣን የመጡት ፕሬዝዳንት ፊሊክስ ሺሴኬዲ ቤተ መንግስት ከገቡ ሀያ ቀን ሳይሞላቸው ነው ዛሬ የውጭ ሀገር ጉዟቸውን የሚጀምሩት፡፡
ሺሴኬዲ የመጀመሪያ የጉዞ መዳረሸቸው ጎረቤት አንጎላ ናት፡፡ ዲሞክራቲክ ሪፓብሊክ ጎንጎ እና አንጎላ ሰፊ የድንበር ቦታ የሚጋሩ ሲሆን የሁለቱ ሀገራት መሪዎች በንድበር አካባቢ ስለሚኖሩ ዜጎች ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ፕሬዝዳንቱ የአየንጎላ ጉብኝታውን እንዳጠናቀቁ ወደ ኬንያ ተጉዘው ከፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬኒያታ ጋር ይገናኛሉ፡፡
ሺሴኬዲ ኬንያን ለመጎብኘት የተነሳሱበት ምክንያት በበዓለ ሲመታቸው ወቅት ኡሁሩ በኪንሻሳ ተገኝተው እንኳን ደስ ያለወ ያሏቸው ብቸኛው የአፍሪካ መሪ በመሆናቸው ወሮታቸውን ለመመለስ ሳይሆን አይቀርም ተብሏል፡፡
አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው ፕሬዝዳንቱ ቃለ መሀላ ሲፈፅሙ ሌሎች የአፍሪካ መሪዎች ተወካዮቻቸውን ሲልኩ ኡሁሩ ግን በአካል ተገኝተው የሺሴኬዲን ደስታ ተጋርተዋል፡፡
ኢዲሱ ፕሬዝዳንት ኮንጎ ብራዛቪልን በመጎብኘት የውጭ ሀገር ጉዟቸውን እንደሚያጠቃልሉ የፕሬዝዳንቱ ፅህፈት ቤት አስታውቋል፡፡
መንገሻ ዓለሙ