loading
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ ዓለም አቀፍ ተቋማትና ዲፕሎማቶች በ”ገበታ ለሀገር” ፕሮጀክቶች ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥቶ ነበር፡፡

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2013 የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ ዓለም አቀፍ ተቋማትና ዲፕሎማቶች በ”ገበታ ለሀገር” ፕሮጀክቶች ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥቶ ነበር፡፡የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ የጀመረችው የ”ገበታ ለሀገር” መርሃ ግብር የሸገር ፕሮጀክት ተከታይ ምዕራፍ ነው።

በኢትዮጵያ ጎርጎራ፣ ኮይሻና ወንጪ የሚገነቡት “የገበታ ለሀገር” ፕሮጀክቶች የአረንጓዴ ኢኮኖሚን ለማሳደግ የሚያግዙ መሆናቸውን ገልጸዋል።በመሆኑን ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በፕሮጀክቶች ላይ በመሳተፍ ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ እድገት የራሳቸውን አሻራ እንዲያሳርፍ ጥሪ አቅርበዋል።የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር አብርሃም በላይ ፕሮጀክቶቹ መንግስት የግል ዘርፉን በማስተባበር ለቱሪስቶች ምቹና ሳቢ ለማድረግ የሚያከናውናቸው መሆኑን ገልጸዋል።

በመሆኑም መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ ዓለም አቀፍ ተቋማትና ዲፕሎማቶችን ጨምሮ ሁሉም በመሰረተ ልማት ማስፋፋት ሥራው ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ አመልክተዋል።የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ በበኩላቸው መንግስት ለፕሮጀክቶቹ ውጤታማነት አስፈላጊ የሆኑ የሃብት ማሰባሰቢያ መንገዶችን ነድፎ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ገልጸዋል።”በመሆኑም በቀጣይ በውጭ ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ዓለም አቀፍ ለጋሽ ተቋማት ሀብት ለማሰባሰብ የሚደረገው ጥረት ቀጣይነት ይኖረዋል” ብለዋል።በኢትዮጵያ የተጀመሩ የገበታ ለሀገር ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ 3 ቢሊዬን ብር እንደሚያስፈልግ ቀደም ሲል መገለጹ ይተዋሳል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *