የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ገዱ ወደ ጁባ አቀኑ፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ገዱ ወደ ጁባ አቀኑ፡፡
የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በ67ኛው የኢጋድ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ልዩ ስብሰባ ለመሳተፍ ዛሬ ጧት ወደ ደቡብ ሱዳን ጁባ ተጉዘዋል።
ዛሬ እና ነገ የሚካሄደው 67ኛው የኢጋድ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ልዩ ሰብሰባ በደቡብ ሱዳን ተደራዳሪ ወገኖች የተደረሰው ስምምነት አፈጻጸም የደረሰበትን ደረጃ በመገምገም የመፍትሄ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ተብሏል።
ምንጭ ፤-የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት