loading
የዘገየው የኢትዮጵያ ቡና ቤተሰባዊ ሩጫ በመጭው እሁድ ይደረጋል

አርትስ ስፖርት 29/02/2011

የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ በሦስተኛው የቡና ቤተሰባዊ ሩጫ ዙሪያ ዛሬ ለመገናኛ ብዙሀን መግለጫ ሰጥቷል፡፡ቤተሰባዊ ሩጫው ዘንድሮ ለሶስተኛ ጊዜ ‹‹ለቡንዬ እሮጣለሁ›› በሚል መሪ ሀሳብ ይካሄዳል ተብሎ ከታሰበው የመሮጫቀን፤ የመወዳደሪያ ማሊያ በተሎ በጊዜ ባለመታተሙ እና ሀገሪቱ ውስጥ በነበረው አለመረጋጋትና ፍቃድ አለማግኘትምክንያት በማድረግ ቢዘገይም በመጨረሻ ህዳር 2/2011 ዓ/ም ከማዳው 1፡00 ጀምሮ እስከ ረፋዱ 5፡00 ሰዓትድረስ የ8 ኪ.ሜ ሩጫ ይካሄዳል ሲሉ የክለቡ ፕሬዚዳንት መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ አስታውቀዋል፡፡ የቤተሰባዊ ሩጫውዋና አላማ በክለቡ ቤተሰባዊ ትስስርን መፍጠርና ማጠናከር እና የገቢ ማግኛ ዘዴ ሲሆን በዘንድሮው ሩጫ ከ30ሺ በላይየሁነቱ ተካፋይ ቤተሰቦች ጥያቄ ቢያቀርቡም 25ሺ ያህል የመሮጫ ማሊያዎች ለአዋቂዎችና ህፃናት የተለያዬበማዘጋጀት በ250 ብር ዋጋ እየተሰራጨ እንደሆነ የደጋፊዎች ማህበር ፕሬዚዳንት አቶ ክፍሌ አማረ ተናግረዋል፡፡ አቶክፍሌ ውድድሩ ከዘር፣ ከሀይማኖትና ፖለቲካ ጉዳዮች ነፃ እንዲሆን እንፈልጋለን ያሉ ሲሆን የሩጫው ተካፋይ ቤተሰቦችለፍተሻ አለመተባበር፣ ከቡና አርማና ባንዲራ ውጭ መያዝና ተገቢ ያልሆነ ፅሁፍ ማስፈር፣ ስለትና ተቀጣጣይ ነገሮችንመያዝ እንዲሁም ሰላምን የሚያውኩ ነገሮችን መያዝ እንዲሁም ህፃናት ብቻቸውን እንዲሮጡ ማድረግ የማይፈቀዱመሆናቸውን ገለፃ አድርገዋል፡፡ በመግለጫው ሩጫው በሰላም እንዲጠናቀቅ ለማስተባበር የተለየ ማሊያ የሚለብሱ300 አስተባባሪዎች እና ሌሎች ደህንነቱን የሚያስጠብቁ አካላት እንደተዘጋጁ ተነግሯል፡፡ በሰላም እንዲጠናቀቅም ጥሪቀርቧል፡፡ ቤተሰባዊ ሩጫው ክለቡ ከሚገኝበት ወረዳ 1 ለቡ – ሚካኤል አደባባይ – ለቡ አደባባይ – ሆፕ ዩኒቨርሲቲይካሄዳል ተብሏል፡፡ ከሩጫው ከ600 ሺ በላይ ገቢ ይገኛል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ለስታዲየም ግንባታና ሌሎችይውላል፡፡ በጋዜጣዊ መግለጫው ወቅት ከጋዜጠኞች በተነሱ ጥያቆዎች ለሌሎች ክለቦች ፈተና የሆነባቸው የገንዘብእጥረት ቡና እንዳያጋጥመው በቀጣይ ምን ለመስራት አንዳቀደ የተጠየቀ ሲሆን ከ17 አመት በታች ታዳጊዎች ላይእንሰራለን፣ በባህር ማዶ ከሚገኙ ደጋፊዎቻችን ተጠቃሚ ለመሆን እና በውድ ከውጭ የሚመጡ የቡናን ማሊያዎችበመሸጥ የውጭ ምንዛሬ ለማምጣት እንደታሰበም መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ አስታውቀዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *