loading
የጋሞ ሽማግሌዎችና አባገዳዎች በቡራዩ የእዉነተኛ እርቅ ምልክት የሆነዉን የእጅ መታጠብ ስነ ስርዓት አካሄዱ

አርትስ 29/01/2011

በቡራዩ ተፈጥሮ የነበረውን ግጭት ተከትሎ የጋሞ ሽማግሌዎችና አባገዳዎች የአካባቢው ማህበረሰብ ግንኙነቱን ወደ ቀደመ ይዞታ ለመመለስ የሚያስችል ባህላዊ ስርዓት  የሆነዉን የእጅ መታጠብ ስርዓትን ከዉነዋል፡፡

ኢቢሲ እንደዘገበው በጋሞ ብሄረሰብ የእጅ መታጠብ ስነ ስርዓት አለመግባባትና ግጭት ሲከሰት ወደሰላማዊነት መመለሻ ባህላዊ ሂደት አድርገው ይመለከቱታል፡፡

የእጅ መታጠብ ስነ ስርዓቱ ከእኩይ ድርጊትና ወንጀል የማንፃት ስራ ተደርጎም ይወሰዳል፡፡

በግጭቱ ምክንያት የተፈጠረውን ቀውስ ተከትሎ በሁለቱም ወገኖች እጅ ላይ ደም እንደሌለ ሽማግሌዎቹና አባገዳዎቹ በመናገር የማቀላቀል ስራ አከናውነዋል፡፡

የጋሞ ሽማግሌዎችና አባገዳዎች ስነ ስርዓቱን በጋራ ፈፅመውታል፡፡

በእጅ መታጠብ ስነ ስርዓቱ ላይ ከቡራዩ ከተማ የተውጣጡ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ታድመዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *