loading
የፈረንሳዩ ኤርባስ ለኢትዮጵያ ገበያ ሄሊኮፕተር እያስተዋወቀ ነዉ

አርትስ 05/02/2011
ኤች 125፣ኤች 160፣ኤች 145 ና ሌሎችም ዘመናዊ ሄሊኮፕተሮች ለገበያ የቀረቡ ሲሆን ፤ሄሊኮፕተሮቹ ለሚሊተሪ አገልግሎት ፤ለድንገተኛ አደጋዎች፤ ለቤተሰባዊ ጉዞዎች
እና ለተለያዩ አገልግሎት እንደሚዉሉ የኤርባስ ሚሊተሪ ሚሽን ስፔሻሊስትና ሴልስ ፕሮሞሽን ማኔጀር ፊሊፕ ኮን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል፡፡
ዝቅተኛዉ የአንድ ሄሊኮፕተር ዋጋ ከ2 አስከ 2.5 ሚሊየነር የአሜሪካ ዶላር የተገመተ ሲሆን እንደሄሊኮፕተሮቹ ዘመናዊነትና የአገልግሎት ልዩነት ዋጋቸዉ እየጨመረ እንደሚሄድ የኤርባስ የአፍሪካ ሴልስ ማኔጀር ጄሮም ዱሞሊን ነግረዉናል፡፡
በኢትጵያ ገበያም የሄሊኮፍተር ፍላጎት እንዳለ ከኤርባስ ሰምተናል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *