loading
ዩጋንዳውዊ አርቲስት እና ፖለቲከኛ ሮበርት ኪያጉላኒ ዳግም እስር ቤት ገባ::

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2013 ዩጋንዳውዊ አርቲስት እና ፖለቲከኛ ሮበርት ኪያጉላኒ ዳግም እስር ቤት ገባ::በቅፅል ስሙ ቦቢ ዋይን እየተባለ የሚጠራው ዩጋንዳዊው የፖፕ ሙዚቃ አቀንቃኝና ተቃዋሚ ፖለቲከኛ ከአሁን በፊትም መንግስትን ተቸህ ተብሎ በተደጋጋሚ ለእስርተዳርጎ ያውቃል፡፡ ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒን አጥብቆ በመተቸት የሚታወቀው ቦቢ ዋይን አዲስ ባቋቋመው ፓርቲ ፅህፈት ቤቱ በፖሊስ ተይዞ መወሰዱን ጠበቃው ተናግረዋል፡፡

ጠበቃው አክለው እንዳሉት የፖሊስ እና የጦር ሰራዊት አባላት ደንበኛቸውን በቁጥጥር ስር ከማዋላቸው በፊት በአካባቢው መንገዶችን ሁሉ በመዝጋት የፓርቲውን አባላት ያዋክቡ ነበር ብለዋል፡፡ አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ በዘገባው እንዳስነበበው ፖሊስ የታሳሪውን ቢሮ በመበርበር በርካታ ዶክመንቶችን
መውሰዱን በስፍራው የነበሩ የዓይን እማኞች ተናግረዋል፡፡

ቦቢ ዋይን በፖሊስ የተያዘው አዲስ ከመሰረተው ከናሽናል ዩኒቲ ፕላትፎር ፓርቲ አባላት ጋር በፅህፈት ቤቱ ስብሰባ ላይ በነበረበት ወቅት ነው ተብሏል፡፡ አርቲስቱ ፖለቲከኛ በመጭው የፈረንጆቹ ዓመት ሀገሪቱ በምታካሂደው ጠቅላላ ምርጫ ለመሳተፍ ዝግጅት እያደረገ ባለበት መታሰሩ በደጋፊዎቹ ዘንድ ብስጭትና ድንጋጤን ፈጥሯል ነው የተባለው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *