loading
ደቡብ አፍሪካ የኮቪድ-19 ታማሚዎች ቁጥር መጨመሩን ተከትሎ ዳግም ወደ ጥብቅ የእንቅስቃሴ እቀባ ተመለሰች::

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 9፣ 2013 ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎዛ በሰጡት መግለጫ በሀገሪቱ ከኮቪድ-19 ጋር በተያያዘ ምክንያት ሆስፒታል የሚገቡ ሰዎች ቁጥር በ59 በመቶ መጨመሩን ይፋ አድርገዋል፡፡ በዚህም የተነሳ የምሽት የሰዓት እላፊ እና የአልኮል ሽያጭ ላይ ገደቦችን መጣል ግድ ሆኖብናል ነው ያሉት ፕሬዚዳንቱ፡፡

የበሽታውን ስርጭት ለመግታት ሲባል ከምሽቱ አራት ሰዓት እስከ ሌሊቱ አስር ሰዓት ያሉ እንቅስቃሴዎች እንዲገደቡ ተደርጓል፡፡ በአደባባይ በሚደረጉ መሰባሰቦችም በአንድ ጊዜ ከ100 በላይ ሰዎች እንዳይገናኙና በአዳራሾች ውስጥ ደግሞ ከ50 ሰዎች በላይ አንድ ላይ መገኘት እንዳይችሉ መመሪያ
ተሰጥቷል ነው የተባለው፡፡

አልጀዚራ እንደዘገበው የመጠጥ ግሮሰሪዎች እና ሆቴሎችም ከቀኑ አራት ሰዓት እስከ ምሽቱ 12 ሰዓት ባለው ጊዜ ብቻ ደንበኞቻቸውን እንዲያስተናግዱ ነው የተፈቀደላቸው፡፡በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በተጠቂዎች ቁጥር ከአፍሪካ ቀዳሚ የሆነችው ደቡብ አፍሪካ እስካሁን ከ1 ነጥብ 7 ሚሊዮን በላይ ዜጎቿ በበሽታው የተያዙባት ሲሆን ይህም ከጠቅላላው አፍሪካ 40 በመቶ ይሆናል፡፡ ደቡብ አፍሪካ በሽታውን ለመቆጣጠር ባደረገችው የክትባት ዘመቻ ከ3 ሚሊዮን በላይ
ዜጎቿ የመጀመሪያውን ዙር ክትባት ያገኙ ሲሆን 480 ሺህ የጤና ባለሙያዎችም እንዲከተቡ አድርጋለች፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *